የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እየሰራሁ ነው ሲል የወላይታ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡

በወላይታ ዞን የገበያ ማዕከል ላይ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ በማህበረሰቡ ዘንድ መደናገጥን ፈጥሯል፡፡የዞኑ የመንግስት ኮምንኬሽን መመሪያ ኃላፊ አቶ ተመስገን ታደሰ ለአሐዱ እንደተናገሩት በገበያ ማዕከሉ የደረውን የእሳት አደጋ በማህበረሰቡ ዘንድ  መደናገጥን የፈጠረ በመሆኑ የጸጥታ ሁኔታውን አስተማማኝ ለማድረግ በተደራጀ መልኩ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከፌደራልና ከክልል ልዩ ኃይል እንዲሁም ከከተማ አስተዳደር እና በየወረዳው ካለው የጸጥታ ሃይል ጋር በመቀናጀት ህብረተሰቡን ለማረጋጋት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡አሁን ላይ የጸጥታው ሁኔታው የሚያሰጋ ባይሆንም በማህበረሰቡ ዘንድ የተፈጠረውን ስጋት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የቅድመ መከላከል እና የጥንቃቄ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል የመምሪያ ኃላፊው፡፡በገበያ ማዕከሉ የደረሰው የእሣት አደጋ በምን ምክንያት እንደተነሳ በማጣራት ወደፊት የሚገለጽ መሆኑን አቶ ተመስገን ተናግረዋል፡፡

*******************************************************************************

ዘጋቢ፡ ቤዛዊት ግርማ

ቀን፡ 17/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply