
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ጥምረት የስርዓተ ምግብ መሻሻል ክፍል ሃላፊ ወ/ሮ እስራኤል ሃይሉ እንዳሉት፣ኢትዮጵያን ጨምሮ 65 ሃገራት ያሉበት የስርዓተ ምግብ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚሰራው ጥምረት በፈረንጆቹ 2030 የስርዓተ ምግብ ችግሮችን ዜሮ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡
ነገር ግን በሃገራችን ኢትዮጵያ የሚታዩ የሰላም ችግሮች ይህንን እቅድ ለማሳካት እንቅፋት ሊሆኑ እንደሚችሉ ወ/ሮ እስራኤል ገልጸዋል፡፡
ጥምረቱ በህጻናት ላይ የሚታየውን መቀንጨር ፤የሰውነት መቀጨጭን እና ሌሎች ከስርዓተ ምግብ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ለመከላከል የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን ጥምረት የተቀላቀላችው ከአስር አመት በፊት መሆኑን የተናገሩት ሃላፊዋ፤ በትግበራው ላይም በርካታ መሻሻሎች እንዳሳየች ገልጸዋል፡፡
በተቀመጠው እቅድ መሰረት ኢትዮጵያ ከስርዓተ ምግብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን እስከ 2023 ዜሮ ለማድረግ አቅዳ እየሰራች እንደምተገኝ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ጥምረት “ሴቭ ዘ ችልደረን” እና የአየርላንድ ኢምባሲን ጨምሮ ከሌሎች ሃገር በቀል እና አለም አቀፍ ተቋመት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ሃላፊዋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በመሳይ ገ/መድህን
የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post