የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁለተኛው ዙር እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀየኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ለኢትዮ ኤፍ…

የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሁለተኛው ዙር እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ

የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም  እንዳሉት፤ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከ617ሺህ ተማሪዎች ከ2 ሺህ በላይ በሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ለመፈተን መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

94በመቶ  ተፈታኞች በመጀመሪያው ዙር ፈተናቸውን እንደሚወሥዱ ሰምተናል።

የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ፈተናው በሁለተኛ ዙር ከሚሰጥባቸው ቦታዎች መካከል በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ፣ ሠሜን ወሎ እና ዋግኽምራ ዞኖች እንደሚገኙበት ታውቋል።

ኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን የጸጥታ ስጋት ካለ የማይፈተኑ ተማሪዎች ቁጥር ከ36ሺ ሊበልጥ እንደሚችልም ተነግሯል በመሆኑም አካባቢው መረጋጋቱ ሲረጋገጥ ፈተናውን በሁለተኛው ዙር ይወስዳሉ ተብሏል።

ጥቅምት 27, 2014 ዓ.ም

መቅደላዊት ደረጄ

Source: Link to the Post

Leave a Reply