የጸጥታ ችግር ፈተና ሆኖብኛል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡አገልግሎቱ በጸጥታ ችግር ምክንያት እቅዶችን ለማሳካት መቸገሩንም አስታውቋል፡፡ በባለፉት 10 ወራት ውስጥ 76…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Hu0zfE-xUOBpUEFRfcgOkP_nupIdUF5Og3m1D3Tn2fETTXCwTZUlfCKs1pSAhy43ACSGZnkzRRcKBpzggTKQZK3AQMZbPqqgqBvDc4-NkGgPORWVn0RYmuoGhyYo0coKuv3GUsp95SbJcImdPUJr4t8bl0KfiL0jQxg2dEAJAxdkaEu4IEwF-jY4TmrkDrwVNnAPSsTzk8-Xu0GM4E4jAxNbLUiQdMy0ZdlO7_abJSKGt94l34KoV5gxQu-LtXWpYVi35Y6fzin-R3CVn7Tnfp4M1izHPcf21HHofMpLrtL7lk-0O_lqQWMGbpVoHv63apf0Fv4VxxiLcs7PpezKTg.jpg

የጸጥታ ችግር ፈተና ሆኖብኛል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ በጸጥታ ችግር ምክንያት እቅዶችን ለማሳካት መቸገሩንም አስታውቋል፡፡

በባለፉት 10 ወራት ውስጥ 76 የሚሆኑ ለአዳዲስ እና ለገጠር መንደሮች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንደተቻለ የተናገሩት የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግት የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ናቸው፡፡

ዳይሬክተሩ እንደገለጹ በሀገሪቱ በሁሉም አከባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን፤ አገልግሎቱ ለ3መቶ 28 ሺህ ከ300 በላይ አዳዲስ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉም ተመላክቷል፡፡

በሚያዚያ ወር በቻ በ11 ቀናት ውስጥ 60 በመቶ ለሚሆኑ ደንበኞች አገልግሎቱን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ነገር ግን አገልግሎቱ የጸጥታ ችግር ዕቅዶች ለመሳካት ፈተና እንደሆነበት ተገልጿል።

በእሌኒ ግዛቸው

ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply