“የጽንፈኞች ስንቅ አቀባይ የሆነው ትሕነግ እየተደመሰሰና በሕግ ጥላ ስር እየወደቀ ባለበት ወቅት የቅጥረኞቹ መወራጨት በኃይል አሰላለፍ ረገድ አንዳች ለውጥ እንደማያስከትልና የሕግ ማስከበሩ ኺ…

“የጽንፈኞች ስንቅ አቀባይ የሆነው ትሕነግ እየተደመሰሰና በሕግ ጥላ ስር እየወደቀ ባለበት ወቅት የቅጥረኞቹ መወራጨት በኃይል አሰላለፍ ረገድ አንዳች ለውጥ እንደማያስከትልና የሕግ ማስከበሩ ኺ…

“የጽንፈኞች ስንቅ አቀባይ የሆነው ትሕነግ እየተደመሰሰና በሕግ ጥላ ስር እየወደቀ ባለበት ወቅት የቅጥረኞቹ መወራጨት በኃይል አሰላለፍ ረገድ አንዳች ለውጥ እንደማያስከትልና የሕግ ማስከበሩ ኺደት በእነሱም ላይ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል።” የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን መግለጫ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን የሰጠው መግለጫ የጽንፈኞች ስንቅ አቀባይ የሆነው ትሕነግ እየተደመሰሰና በሕግ ጥላ ስር እየወደቀ ባለበት ወቅት የቅጥረኞቹ መወራጨት በኃይል አሰላለፍ ረገድ አንዳች ለውጥ እንደማያስከትልና የሕግ ማስከበሩ ኺደት በእነሱም ላይ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። በዋናነት የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስት ችግሩን የመፍታት ኃላፊነት እንዳለበት ሊገነዘብ ይገባል። የአማራ ሕዝብ አገራችንን ለማፍረስ ዝግጅቱን አሰናድቶ ጦርነት የከፈተውን የትሕነግ ኃይል በመግጠም እየተዋደቀ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በየስርቻው የተወሸቁ አልባሌ ጽንፈኞች ጉዳት እንዲያደርሱበት ሊፈቀድ አይገባም። የፌዴራል መንግስት፣ የቤኒሻንጉል ክልላዊ መንግስትና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተውን ያልተቋረጠ ዘር ተኮር ጥቃት በዘላቂነት ለማስቆም አስቸኳይ የሆኑ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጠው ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። በጽንፈኛ ኃይሎች በተደጋጋሚ በተከፈቱ ዘር ተኮር ጥቃቶች የደረሱትን ጉዳቶች በማጣራት ጥፋተኞችን በዘር ማጥፋት ወንጀል ማእቀፍ ስር ተጠያቂ ማድረግም ይገባል። አጠቃላይ የትሕነግን በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወድህ ያለውን ሥምሪት ስንመረምር ግልፅ የሆነ አገር በቀል የሽብር ድርጅት መሆኑን እንረዳለን። በርግጥ አሁን ትሕነግ ከዓለምአቀፍ የሽብር ድርጅቶች ጋር በከፍተኛ ቅንጅት እንደሚሰራም ይታወቃል። ቤንሻንጉልና ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ካሉ ጽንፈኛ ኃይሎች በተጨማሪ አልሸባብና አይ ኤስ አይ ኤስ ጋር ጭምር በትብብር እየሰራ ስለመሆኑ ማስረጃዎች እየወጡበት ይገኛል። አብን ድኅረ ትሕነግ የኢትዬጵያ የፖለቲካ ብሩኅ እንደሚሆንና ለረጅም ዘመን መንበሩን ተቆናጥጦ የቆየውን የጥላቻ ድባብ በመግፈፍና በምትኩ ፍቅር፣ ፍትኅ፣ እኩልነት፣ ዴሞክራሲና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለሚንቀሳቀሱ በጎ ጥምረቶች መንገድ እንደሚጠርግ ይገነዘባል። ለዚህም ሁሉም አገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አብን ጥሪውን ያቀርባል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply