የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በኢትዮጵያ ጉዳይ

https://gdb.voanews.com/c0d95122-b015-4515-84d4-63d15dcaf38b_tv_w800_h450.jpg

ትናንት ምሽት  በኢትዮጵያ ጉዳይ በተካሄደው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛና የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፤ ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ ማምጣት የሚቻልበት ጊዜ እየተሟጠጠ በመሆኑ አስቸኳይ ርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ገለፁ።  

የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሃት አመራሮች ልዩነታቸው ፖለቲካዊ መሆኑንና ፖለቲካዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው በግል እንደሚያምኑ ይፋ አድርገዋል፡፡  

የእርሳቸውን ሪፖርት ተከትሎ የምክር ቤቱ አባላት ባደረጓቸው ንግግሮች እንደወትሮው የተለያዩ አቋሞችን አንጸባርቀዋል፡፡  

“ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሔ ይፈለግ” ለሚለው ሐሳብ ኢትዮጵያ ክብር እንዳላት የገለጹት በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፣ ህወሃት ከተለያዩ አካላት በግልጽ ድጋፍ እንደሚያገኝ አብራርተው በዚህም ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ህወሃት መሰል ውንጀላዎችን ማስተባበሉ ይታወቃል፡፡ 

Source: Link to the Post

Leave a Reply