የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/5FA3/production/_120238442_dead188d-de59-4826-9c5d-4d2b6991c330.jpg

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እየተባባሰ መሄዱ በጽኑ እንዳሳሰበውና በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቀረበ። አርብ ምሽት ከተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ በኋላ በአስራ አምስቱም አባላቱ ተቀባይነት አግኝቶ በወጣው መግለጫ ላይ ሁሉም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ጦርነቱን በማቆም “ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ የተኩስ አቁም ለማድረግ” ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply