የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ሕብረት እያደረገ ላለው የሰላም ጥረት ድጋፉን ሰጠ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/5FA3/production/_120238442_dead188d-de59-4826-9c5d-4d2b6991c330.jpg

በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተውና አንድ ዓመት ያስቆጠረውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማርገብ በተጠራው የፀጥታው ምክር ቤት ጉባዔ የአፍሪካ ሕብረት እያደረገ ላለው የሰላም ተነሳሽነት ድጋፍ ተሰጥቷል። ይህ ድጋፍ የተሰጠው የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት እና ከትግራይ አመራሮች ጋር ድርድሩን አስመልክቶ የነበረው ውይይት በበጎ መልኩ ተቀባይነት ማግኘቱን ከገለጹ በኋላ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply