የፈረስ መድሃኒትን ለኮቪድ ህክምና የወሰዱት ሆስቲፓል ገቡ

https://gdb.voanews.com/A0B8E724-ABA0-48C8-B0D9-2D761559749C_w800_h450.jpg

የአሜሪካ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ኮቪድ 19ን ለመከላከል ለፈረሶች የተዘጋጀውን “አቨርመስትን” የተባለ መድሃኒት በግላቸው ወስደው፣ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ሆስታል የገቡ ህሙማን እንዳሉ በርካታ መረጃዎች የደረሱት መሆኑን በመግለጽ አስጠንቅቋል፡፡

ድርጅቱ ትናንት ቅዳሜ፣ በትዊተር ገጹ ላይ፣ አቨርመስትን የተባለውን የከብቶች መድሃኒት ለሚወስዱት ሰዎች “ እናንተ ፈረሶች አይደላችሁም፡፡ እናንተ ላሞች አይደላችሁም፡፡ ከምር፣ ሁላችሁም ይህን ነገር አቁሙ!” የሚል ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፡፡

የድርጅቱ ማስጠንቀቂያ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚሲሲፕ ክፍለ ግዛት የጤና መምሪያ ያወጣውን ተመሳሳይ መግለጫ ተከትሎ ነው፡፡

የጤና መመሪያው መግለጫ፣ ኮቪድ 19ን ለመከላከልም ሆነ ከህመሙ ለመዳን ፣ የከብቶቹን መድሃኒት በመውሰድ ከታመሙ ሰዎች ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ፣ የ9 1 1 ፣ የድረሱልኝ የስልክ ጥሪዎችን መመዝገባቸውን አመልክቷል፡፡

ከደረሱ የእርዳታ ጥሪ ስልኮች ውስጥ፣ 70 ከመቶ የሚሆነው፣ ለከብቶች የተዘጋጀውን መድሃኒት ወስደው ከታመሙ ሰዎች መሆኑም ተገልጿል፡፡

ሰዎች ስለኮቪድ 19 የተሳሳተ መረጃ በመስማት ራሳቸው ከሚጎዱ እምርጃዎችም እንዲታቀቡ የምግብና መድሃኒት አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡

በሌላም በኩል እንግሊዝ፣ ከመጭው ማክሰኞ ጀምሮ፣ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑና እስከ 8ሺ በሚደርሱ ሰዎች ላይ ኮቪድን መቋቋም የሚያስችል፣ ተፈጥሯዊ የበሽታ ተከላካይ ህወሳት ምርመራን እንድምታደርግ አስታውቃለች፡፡

የእንግሊዝ መንግሥት ዜና ማሰራጫዎች እንደዘገቡት፣ በከኮረና ቫይረስም ሆነ ለተለዋዋጭ ቫይረሶቹ የተጋለጡ ሰዎች፣ ስለሚኖራቸው ተፈጥሯዊ መከላከያ የበለጠ መረጃ ለመሰብሰብ እንደሚፈልጉ ተመልክቷል፡፡ 

ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply