የፈንቅል ሊቀመንበር የነበረው መ/ር የማነ ንጉሴ በትሕነግ ታጣቂዎች መገደሉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ መ/ር የማነ ንጉ…

የፈንቅል ሊቀመንበር የነበረው መ/ር የማነ ንጉሴ በትሕነግ ታጣቂዎች መገደሉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መ/ር የማነ ንጉ…

የፈንቅል ሊቀመንበር የነበረው መ/ር የማነ ንጉሴ በትሕነግ ታጣቂዎች መገደሉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መ/ር የማነ ንጉሴ ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2013 ከሰአት ከመቀሌ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ሒዋነ በተባለች አካባቢ ነው በትሕነግ ርዝራዥ ታጣቂዎች የተገደለው ተብሏል። መ/ር የማነ ህወሓትን በመታገል ትልቅ አስተዋፅኦ የነበረው ደፋር ታጋይ እንደነበር የጠቀሰው ግዕዝ ሚዲያ ጁንታው ከወደቀ በኋላ የሰብአዊ ስራ ለመስራትና ህዝቡ እርዳታ እንዲደርሰው ፣አንቡላንስ ላጡ ነፍሰጡር እናቶች የግለሰብ መኪና በመለመን ወደ ህክምና በማድረስ ህዝባዊ ስራ እየሰራ ነበር ሲልም አክሏል። ወደ ሒዋነ በማቅናት የሰብአዊ ስራ ለመስራት እየሄደ ሳለ በድንገት ስለመገደሉ የዘገበው ግዕዝ ሚዲያ ነው። መ/ር የማነ ንጉሴ የትሕነግን ገመና በስፋት ሲያጋልጡ ከነበሩት መካከል አንዱ ሲሆን የበፊቱ እንዳለ ሆኖ በተለይ በትሕነግ ላይ እርምጃ ከተወሰደበት ማግስት ጀምሮ ግን ከአፈና እና ጭቆና በከፍተኛ መስዋዕትነት ነጻ ስለወጡት ስለወልቃይት፣ ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ ሲያራምደው የነበረው ሀሳብ ከትሕነግ አካሄድ የተለዬ አይደለም በሚል ከተለያዩ አካላት ወቀሳና ትችት ሲቀርብበት እንደነበር ይታወሳል። ነፍስ ይማር! መፅናናትን ተመኘን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply