የፊልም ስክሪፕት እና የስራ ሐሳብ ላላቸዉ ገንዘብ አቀርባለሁ – አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማሕበር በ21 ሚሊየን የተከፈለ ካፒታል ጥቅምት 12/2015 ዓ.ም…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/YVEHbaTV6SC-4cErKsiBv7TGi-RyrA_ur4famS8VfeN4DWZcKZsOQQ0nk_TuAo7j_QC1MYqlFI6eOScStBL4acZUydQkzkH5QDH8osIGsJNFV8k7vp3Bn36CPRFrD7cFMqQHRv9tcnEAtulinoPoKF1CKr8YJff_wBpUqJ_aCkgXLroUUhqgtfzhVEG3U-DlohvFTR8CtU_oNXzbeebtaoLBmR_OHsYVwG-xLWbWmggUBghd99GqqfjKg6hxVugeomml4Ha9P2YbPR0FNZHra_G9QA17VqRkuebpfMk05EmVPwfClPH-ILUAmGeqg3EAkt6Mv6sOJGGU1wCsMFL66w.jpg

የፊልም ስክሪፕት እና የስራ ሐሳብ ላላቸዉ ገንዘብ አቀርባለሁ – አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማሕበር በ21 ሚሊየን የተከፈለ ካፒታል ጥቅምት 12/2015 ዓ.ም በደብረ ብርሐን ስራ እንደሚጀምር አስታዉቋል፡፡

በ33 ሚሊየን የተፈረመ ካፒታል ወደ ገበያዉ መግባት የቻለዉ አኩፋዳ፣ ሴቶችን እና ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ያላቸዉን የተለያዩ አይነት አማራጮችን ይዞ መምጣቱን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሮቤል ንጉሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡

ገበያዉን “ስኬትን በተግባር” በሚል መርሕ ለመቀላቀል የተሰናዳዉ አኩፋዳ፣ በስድስት አደራጆች እና በ1 ሽህ 886 ባለ አክሲዮኖች መቋቋሙ ታዉቋል፡፡

ዋና መስሪያ ቤቱን እና የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በደብረ ብርሐን ይከፍታል የተባለዉ አኩፋዳ፣ ስራ በሚጀምርበት የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸዉ ታላላቅ እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ሮቤል አስታዉቀዋል፡፡

በስድስት ወራት 30፣ በአመቱ መጨረሻ ደግሞ 50 ቅርንጫፎችን ለመክፈት ውጥን የያዘዉ ማይክሮ ፋይናንሱ፣ በ3 አመታት ዉስጥ ተጠቃሽ ያደርገኛል ያላቸዉን አሰራሮች ይዞ ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅት ማጠናቀቁንም ይፋ አድርጓል፡፡

የሐገራችን የፋይናንስ ዘርፍ ችግሮች ከፖሊሲም ጭምር ማነቆ ያለበት መሆኑን የተናገሩት አቶ ሮቤል፣ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በበርካታ የሐገራችን አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማስፋት እንደሚሰራም አስታዉቀዋል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ጥቅምት 09 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply