You are currently viewing የፊደል ሓዋርያ ቦርድ – ጋዜጣዊ መግለጫ (ዶ/ር ኣበራ ሞላ)

የፊደል ሓዋርያ ቦርድ – ጋዜጣዊ መግለጫ (ዶ/ር ኣበራ ሞላ)

ጋዜጣዊ መግለጫ

ነሓሴ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. (September 5, 2020)

የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር (ኣብሻ) የተባለው ድርጅት እ.ኤ.ኣ. በ1982 ዓ.ም. በኮሎራዶ እስቴት፣ ዩናይትድ እስቴትስ የተቋቋመ ነው። ባለፉት 38 ዓመታት የእዚህ ድርጅት ባለቤትና CEO ዶ/ር ኣበራ ሞላ የግዕዝ ፊደልን ኮምፕዩተራይዝ ኣድርገውና ተንከባክበው ሲያሳድጉት ቆይተዋል። እስከ ዛሬ ድረስም ኣራት የዩናይትድ እስቴትስ እና ሦስት የኢትዮጵያ ፓተንቶችን በማግኘት የኢትዮጵያን መብት ኣስጠብቀዋል።

 

በተለይም ባለፉት 30 ዓመታት እነዚህ የግዕዝ ፊደላት እና ፊደላቱን የሚጠቀሙ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከየኣቅጣጫዎቹ በጣም ከፍተኛ ጥቃት ሲደርስባቸው ቆይቷል። ፊደላቱ ከኣስፈላጊው በላይ በዝተዋል በማለት ለመቆራረጥና ለመቀናነስ፣ በኣደባባይም ሆነ ውስጥ ውስጡን ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። በተለይም ዓማርኛን ለማዳከም፣ በዓማርኛ ቋንቋ መናገርና በተሟላ ፊደሎቹ መጻፍ ቀርቶ በላቲን ፊደል እንዲተካ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።

ይህ ጥቃት እንዳይቀጥል ጥንታዊው የኢትዮጵያ የግዕዝ ፊደል ታሪካዊ ቦታውን መያዝ ይኖርበታል። በሥርዓቱ ኮምፕዩተራይዝ የተደረገው ተጠናክሮ ሥራውን በሚገባ መቀጠል እንዲችል፣ ተገቢውን ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል። ይኸንንም ለማጠናከር በእ.ኤ.ኣ. ኤፕሪል ኣራት 2016 የተጀመረው Ethiopic Foundation የሚባል ድርጅት በኣዲስ መልክ ተደራጅቶ በ13 የቦርድ ኣባላት ተቋቁሟል። የመጀመሪያ የፊደል ሓዋርያ ስብሰባውንም በእ.ኤ.ኣ.ሜይ ሃያ ስድስት 2020 ኣድርጓል።

የድርጅቱ ዓላማ የግዕዝን ፊደሎችና ተጠቃሚ ቋንቋዎቹን መንከባከብ፣ ፊደሉን ሳይንሳዊ ማድረግ፣ ቴክኖሎጂው በፓተንቶች እንዲጠበቅ ማበረታታት፣ ዓመታዊ ስብሰባ ማድረግ፣ ለግዕዝ ባለውለታዎች ዕውቅና መስጠት፣ ግዕዝን የኣፍሪቃ ቋንቋዎች መጻፊያና ዓማርኛን ኣሕጉሩ እንዲጠቀምበት ማስፋፋት ይገኙበታል።

ለተጨማሪ መረጃ የድርጅቱ ኢሜይል [email protected] ሲሆን ኣድራሻውም 10145 E. 143rd Way, Brighton, CO 80602, USA ነው።

የፊደል ሓዋርያ Ethiopic Foundation ቦርድ

 

መስተጋህደ ዜና

ዝንቱ ኢትዮጵያ (ኣብሻ) ተጽሕፈ በመንግሥተ ኮለራዶ በአሰርቱ ወተሳቱ ምዕት ሰማንያ ወክሌቱ ዓ/ም። ወበ ዝንቱ ዓመት ተደመረ ቦቱ መስቄ ምዕናም (ልጎት) “Software” ዘ ኢትዮጵያ። ወእምድህረ ዝ ሊቅ ኣበራ ሞላ አግደምደሞሙ ፊዳለተ ግዕዝ ወአልኮሞሙ ኀበ መንኮራኩረ (ምሥዋራተ) አዕምሮ ዘሀጺን (መአሐ) ወተወክፈ አርባእቱ አሜሪካውያን ወሰለሰቱ ኢትዮጵያውያን ምስትጉቡአት (ምግድምዳማት) “Patterns”።

ወእምዝ ቆናጽል እለ አንስኡ ሰኮናሆሙ ላዕለ ሀገሪትነ ቅድስት ወዓባይ ኢትዮጵያ አኀዙ ከመ ያማስኑ ገጻ ለኢትዮጵያ ወይጠይሱ ፊደላቲነ ወያህጽጹ ኍልቆሙ ለሆህያቲሆሙ። ድህሩ ወአረዩ  ግብርናተ ከመ ያግርሩ ርእሶሙ በመናግንንተ ሀጺን ዘግብርናት ወፈተው ከመ ያዔሙ ፊደላተ ላቲን ህየንተ ፊደላተ ግእዝ። ወስእኑ ከመ ይዕቀቡ ግእዘነ ዘተመጦነ አበዊነ ኃያላን ወጽኑአን ኢትዮጵያውያን እለ ይሄይልዎሙ ለመራድያን ለነዋህ መዋዕል።

ወበእንተ ኩሎሙ ጸዋትወ መከራ ዘአጾሩነ እሙንቱ መናፍቃን ወከሀድያን መሠረትነ ወአቀምነ ጉባዔ በአርባእቱ እለት ዘወርሀ ሚያዝያ ክሌቱ እልፍ አሰርቱ ወስድስቱ ዓ.ም. ከመ ይቤዙ ወይዕቀብ ፊደላቲነ ወልሳናቲነ እም አማሲኖቶሙ ለቆናጽል እለ አቅለሉ ክብሮሙ ወአንቀልቀሉ መሠረታቲነ ወአትሀቱ ሰብእናዚአሆሙ።

እግዚአብሄር አምላከ አበዊነ ለይቀባ ለሀገሪትነ ቅድስት ወዓባይ ኢትዮጵያ። ወለነሂ ይጸግወነ ኃይለ ወልቡና ወጥበበ  ከመ ንዕቀብ ትውፊተ ግእዘነ ዘተወከፍነ እም አበዊነ ኃያላን ኢትዮጵያዋያን እለይትመሀጸኑነ  ከመ ንሁር በፍናዊሆሙ ወንጽናዕ በአሰሮሙ።

ኦ አንትሙ ኢትዮጵያውያን እለ ትፈትው ከመ ታእምሩ በእንተ ተቋምነ፤ ትክሉ ትሰአሉነ በዝ [email protected] ድረገጽ።

መራሄ ግብር ዘተቋም

መስቄ ምዕናም (ልጎት) (Software)

መንኮራኩረ (ምሥዋራተ) አዕምሮ ዘሀጺን (መአሐ) (Computer)

ምስትጉቡአት (ምግድምዳማት) “Patterns”።

News Release

September 5, 2020

In 1982 ABSHA was registered with the State of Colorado, USA and Ethiopian Computers & Software was added as an Ethiopic software company. Since then Dr. Aberra Molla, its CEO has computerized Ethiopic and received four USA and three Ethiopian patents.

In spite of these, Ethiopic and its user-languages have been under attack from different directions. With the false excuse that the Ethiopic characters were too many, there were numerous attempts over the last century to reduce the number of characters that existed for thousands of years. Some even cut the characters themselves to pieces. In an attempt to weaken the Amharic language, certain groups of people were discouraged not to talk or write in Amharic.  Instead, using Latin alphabets was highly encouraged.

Ethiopic Foundation which was established on April 4, 2016 has recently been reorganized with 13 board members. The aim of the Foundation is to nurture Ge’ez and the several Ethiopian languages that use it. Computerizing the Ge’ez alphabet scientifically, is one of the goals of the Foundation so that all of its user languages could easily utilize the available technology.

Computerizing the Ge’ez and the many languages using it and protecting the invention with several patents was a daunting task that Dr. Molla has single-handedly undertaken for the last 38 years.

To encourage Ge’ez to be widely used and recognizing those who promoted it is another goal of the Foundation. Holding annual meetings to broaden users and supporters is also one of its duties.  The Ethiopic alphabet is probably the best user-friendly writing system that has a character for practically any phoneme or sound. Promoting the Ge’ez alphabet as a writing system for African languages is one of the objectives to be pursued by the Foundation with Amharic as a common language.

For more information, email the company at [email protected] 10145 E. 143rd Way, Brighton, CO 80602, USA

Board of Directors

 

 

Leave a Reply