የፋሲካ ባዘር እና ኤክስፕ በሚሊንየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው

ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ያሰናዳው ፋሲካን በሚሊንየም ባዛር እና ኤክስፖ ሀሙስ ሚያዚያ 10 ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል ።

ባዛር እና ኤክስፖው ከሚያዛ 10 እስከ 26 2016 አመት ድረስ ለተከታታይ 17 ቀናት የሚቆይ ነውም ተብሏል።

በዚህ አውደ ርዕይ በአልን አስታኮ የሚመጡ የእቃዎች መወደድን የሚቀርፍ ሲሆን ሸማቹን ቀጥታ ከሻጩ የሚያገናኝ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ለተከታታይ 10 ቀናት በሚቆየው በዚህ የንግድ አውደ ርዕይ ላይ ከሁለት ሺህ በላይ የተለያዩ ነጋዴዎች እንደሚገኙ ነው የተነገረው።

እንደዚሁም የምግብ እና የአልባሳት ምርት አቅራቢዎች ፣ የስጦታ እቃዎች ፣ የቤት እና የቢሮ መገልገያ የሚገኝበት የንግድ አውደ ርዕይ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን በቀን ከአስር ሺህ በላይ ጎብኚዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ ባዛር ገዥና ሻጭን፣ አምራች እና ሸማቹን በአንድ የሚያገናኝ ሲሆን ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በባዛሩ ላይ የመጋዘን ኪራይ ከ35 ሺህ ብር ጀምሮ እንደሆነና ባዛሩ ላይ ከ27 በላይ ድምፃዊያን እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

ለአለም አሰፋ

መጋቢት 26 ቀን 2016

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply