የፋሲካ ባዛርና ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከፈታል

የፋሲካ  ባዛርና ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከፈታል

ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ፣ ከሚያዚያ 10 እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ  የፋሲካ  ባዛርና ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

ለ20 ቀናት ገደማ ክፍት የሚሆነው ባዛርና ኤክስፖ፤ ሸማቹ በተመጣጣኝና ቅናሽ ዋጋ ከራሱ ከአምራቹና አስመጪው የሚገበያይበት ነው የተባለ ሲሆን፤ አምራቹም ከሸማቹ ከፍተኛ ገበያ የሚያገኝበት እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

ከ2ሺ በላይ አስመጪና ሻጮች እንደሚሳተፉበት በተነገረለት በዚህ ባዛርና ኤክስፖ፤ በቀን እስከ 10ሺ የሚደርሱ ሸማቾች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዚህ ባዛርና ኤክስፖ ከዓውዳመት ሸቀጦች በተጨማሪ፣ በየቀኑ ታዋቂ ሙዚቀኞች፣ ተወዳጅ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡

የፋሲካ ባዛርና ኤክስፖ የፊታችን ሚያዚያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ባለሃብቶች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በይፋ ይከፈታል ተብሏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply