የፋኖንን ንቅናቄ በፖለቲካ ድርጅት ቁመት ልክ ለማስላት የመጣደፍ ስሁትነት ————— ሸንቁጥ አየለ ————- አለፋኖዎች የጋራ ስምምነት የፋኖንን ንቅናቄ በፖለቲካ…

የፋኖንን ንቅናቄ በፖለቲካ ድርጅት ቁመት ልክ ለማስላት የመጣደፍ ስሁትነት ————— ሸንቁጥ አየለ ————- አለፋኖዎች የጋራ ስምምነት የፋኖንን ንቅናቄ በፖለቲካ ድርጅት ቁመት ልክ አስልቶ ለማስገባት ወይም ደግሞ በአንድ የፖለቲካ ስብስብ ስር ብቻ ጠርንፎ ለመዋጥ መሞከር አደጋ ነው::… ምክንያቱም የፋኖዉ ንቅናቄ ህዛብዊ መሰረት ስላለዉ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል:: ህዝባዊ መሰረት ያለዉን ንቅናቄ የምታስተሳስረዉና የምትመራዉ በፍቅር:በማግባባት እና በማሳመን ብቻ ነው::እያንዳንዱን ቀበሌ : እያንዳንዱን ወረዳ እያንዳንዱን ክፍለሀገር አግባብተህ አክብረህ አፍቅረህ መያዝ የመጀመሪያዉ የህዝባዊ ንቅናቄ መሪ ስራ ነዉ::አንዳንድ ቡድኖችም እንቢ አንሰባሰብም ቢሉህ እንኳን ሳትታክት ለማግባባት መጣር እንጂ ወደ ሀይል የሄድህን እንደሆነ አከተመልህ:: ህዝባዊ መሰረት ያለዉን ንቅናቄ ለመምራት ያለህ አንድ ብቸኛ መሳሪያ ራዕይዉን ከፍ አድርጎ በመስቀል ሁሉም ወደ ራዕይዉ እንዲሳብ ማድረግ ነዉ:: ህዝባዊ መሰረት ያለዉ ንቅናቄ ማለት ምን ማለት ነዉ ብለህ የጠየቅህ እንደሆነ እጅግ አስደማሚ ነገር ታገኛለህ::ልክ ወደ ንብ ቀፎ ተጠግተህ አንዲቷን ንብ በጅህ ይዘህ ልትቆጣጠራት ስትሞክር የቀፎዉ ንቦች ወደ አንተ እንደሚወረወሩት ማለት ነዉ:: አንዲቷን የንብ ቀፎ በአንድ ቀበሌ ህዝብ መስላት::አለፍላጎቱና አለ ፈቃዱ የሚሰበሰብ ህዝባዊ መሰረት ያለዉ ንቅናቄ ከቶም በምድር ላይ በሰዉ ልጆች ታሪክ ዉስጥ አልተዘገበም:: እናም የዚህ መሰሉ የህዝባዊ ንቅናቄ መሪ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ፍቅር ያስቀድም::ሌሎችን ማክበርን ይማር::ደጋግሞ ደጋግሞ ማወያዬትን ይልመድ:: ብሎም ህዝባዊዉን ንቅናቄ ወደ አንድ ማዕከል ለመሰብሰብ የሚያስችል ከፍ ያለ ሳቢ ራዕይን በታላቁ የመሰባሰቢያ ማማ አናት ላይ ይስቀለው:: በተለይም የፋኖንን ንቅናቄ በፖለቲካ ድርጅት ቁመት ልክ ለማስላት የመጣደፍ ስሁትነት በፍጥነት ይታረም:: በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መጻፍ ፈልጌአለሁ::አሁን ግን ስለደከመኝ ጽሁፌን እዚህ ጋ ልግታዉ:: ለማጠቃለያ ግን እምነት ያለህ ሁሉ ልብ በል:: ፋኖዉን ያስነሳዉም ያደራጀዉም በአንድ መንፈስ ያስተሳሰረዉም እግዚአብሄር ነዉና ይሄን አስተዉል::እግዚአብሄር ፋኖዉ ላይ አላማ አለዉና ሁሉ ነግር በማስተዋል ይሁን::ይሄ ነገረ እግዚአብሄር ካልተዋጠልህም ችግር የለዉምም::በዉድቀትህ እግዚአብሀር እንድትዉጠዉ ያደርግሃልና:: ማንህም ተንኮል በልብህ የሸመቅህ እንደሆነ ግጭትህ ከእግዚአብሄር አላማ ጋር መሆኑን እንዳትረሳ ! ስለሆነም ፍቅር : መነጋገር:ሳይታክቱ መወያዬት: መከባበር ብሎም ከሁሉም በላይ ሁሉም ወደ ከፍ ወዳለዉ የጋራ ራዕይ ላይ እንዲመለከት ከፍ ያለዉ ሳቢ እና አሰባሳቢ ራዕይ በታላቁ የመሰባሰቢያ ማማ አናት ላይ ይስቀል:: —– ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይታደጋት !

Source: Link to the Post

Leave a Reply