የፋኖ ብርሀኑ ፈረደ የእርዳታ ጥሪ ከጎንደር አሻራ ሚዲያ ጥር 17 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር በወልቃይት ጠገዴ ደጀና በኩል ትሕነግን በመደምሰስ ረገድ ከፍ…

የፋኖ ብርሀኑ ፈረደ የእርዳታ ጥሪ ከጎንደር አሻራ ሚዲያ ጥር 17 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር በወልቃይት ጠገዴ ደጀና በኩል ትሕነግን በመደምሰስ ረገድ ከፍተኛ ተሳትፎ ካደረጉት ታጋዮች መካከል አንዱ የሆነው ፋኖ ብርሃኑ የወገን ሁለንተናዊ ድጋፍ በእጅጉ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡ በትሕነግ ላይ ትግሉን ሀ ብሎ የጀመረው “አማራ ነኝ!” ብሎ በመታገል መሆኑን የገለፀው ፋኖ ብርሃኑ ፈረደ በወልቃይት ጠገዴ ዳንሽ ላይ በስርዓቱ እስርና እንግልት ይደርስበት እንደነበር አውስቷል። እንደአብነትም ከፋኖ ጎይቶም እርስቃይ፣ ከፀጋዬ ፈለቀና ከሌሎችም ጋር በመሆን በ2008 ከእነ አርበኛ ጎቤ መልኬና ከእነ ሻለቃ ደጀኔ ማሩ ጋር በመቀላቀል በጫካ ሆነውም ታግለዋል።ወልቃይት ጠገዴ ወንዱን ሳይሆን መሬቱንና ሴቱን ብቻ ነው የምንፈልገው የሚለው ትህነግአማራን በጠላትነት በመፈረጅ ወደ አዲስ አበባ ማዕከለዊ እና ቂሊንጦ ተወስዷል፤ ለ3 ሰዓዕታት ያህል በግፍ ተሰቅሎ የግፍ ምርመራ ተደርጎበታል። ከትግል አጋሮቹ ጋር ሆኖ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት እና የወሰን ጥያቄን በማቅረቡ አሸባሪ ተብሎ የሀሰት ምስክር ተዘጋጅቶለት ከተሰቃየ በኋላ በህዝብ ተጋድሎ መፈታቱንም አውስቷል። እነ ፋኖ ጎይቶም እርስቃይ እና ብርሃኑ ፈረደ በ2010 ዓ.ም ከተፈቱበት ቀን ማግስት ጀምሮም ትሕነግ በአማራ ላይ የሚፈፅመው ጥቃት የቀጠለ መሆኑን በመገንዘብ በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ የሀይል አመራር በመሆን ሲታገሉ ቆይተዋል። ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ማክሰኞ ገበያን (ከተማ ንጉስን) ከትህነግ ነጻ ካወጡትና በመቀጠልም ወደ ደጀና በማቅናት ትህነግን ካሳደዱት ተጠቃሽ የሆነው ፋኖ ብርሃኑ ፈረደ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም መቁሰሉን ጠቅሷል። ፋኖ ብርሃኑ ፈረደ በደረሰበት ጉዳት አሁን ላይ ከነርብ ጋር የተያያዘና ጥይቱም ያልወጣለት በመሆኑ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ እንዲታከም ሲል የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈር የጻፈለት ቢሆንም እስካሁን ድረስ በመንግስት በኩል ተገቢ የሆነ እውቅና እና የህክምና ድጋፍ አልተደረገልኝም ብሏል። በጎንደር ከተማ የሚገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦች ግን አቅማቸው በፈቀደ መጠን በማገዝ ከጎኔ አልተለዩኝምና ላመሰግናቸው እወዳለሁ ብሏል። ፋኖ ብርሃኑ በህግ ማስከበር እርምጃ ላይ ሳለ የቆሰለ በመሆኑ ለህክምና ድጋፍ ይደርግለት ዘንድ ለአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ደብዳቤ አስገብተው እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል። ባለቤቱን ጨምሮ 3 ህጻናት ያሉት ፋኖ ብርሃኑ ያጋጠመውን አደጋ መንግስት ብሎም በሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያሉ በጎ ፈቃደኛ ወገኖች ሁሉ ህይወቱን እንዲታደጉት ጥሪ አቅርቧል። ብርሃኑ ፈረደን በማስታመም ላይ የሚገኘው ፍስሃ ፈረደ የችግሩን አሳሳቢነት ገልጾ የሁላችንም እርብርብ አስፈላጊነት መሆኑን ጠቅሷል፤ የበለጠ ግን መንግስት በትግሉ ላይ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉና የቆሰሉ ታጋዮችን በእኩል ዓይን ተመልክቶ እንዲደግፋቸው ጠይቋል። ፋኖ ብርሃኑ ፈረደን ለመደገፍ ለምትፈልጉ በወንድሙ በኩል ማለትም ፍስሃ ፈረደ ብላችሁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000335168163 መርዳት የምትችሉ መሆኑን አስታውቀዋል። ስልክ ቁጥር 091 804 0351 በመደወል ግኘት እንደሚቻል አስታውቋል፡፡ ምንጭ ፡- አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)

Source: Link to the Post

Leave a Reply