You are currently viewing #የፋኖ ጥሪ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ በሃሰት የተወነጀሉት  የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር አመራሮችና አባላት  ነገ  ጠዋት ፍ/ቤት ይቀርባሉ‼️ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 የአማራ…

#የፋኖ ጥሪ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ በሃሰት የተወነጀሉት የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር አመራሮችና አባላት ነገ ጠዋት ፍ/ቤት ይቀርባሉ‼️ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 የአማራ…

#የፋኖ ጥሪ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ በሃሰት የተወነጀሉት የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር አመራሮችና አባላት ነገ ጠዋት ፍ/ቤት ይቀርባሉ‼️ 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በሃሰት ውንጀላ ፣በመንግስት ተብየው የተለመደ ሴራና ተንኮል በግፍ የታሰሩ ጓዶቻችን ነገ ማለትም አርብ 08/11/2014 ዓ.ም የአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት በጠዋቱ 2:00 ሰዐት ይቀርባሉ። በመሆኑም ፦ 1).ጀግናው የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር የጋሸና ዘማቾችና በድል የተመለሱ አባላት እና የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች በሙሉ 2) . ተተኪው አናብስት የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በሙሉ 3).የተከበረከው ፣ቆራጡ እና አይበገሬው የባሕር ዳር ከተማ እና አካባቢው አማራ ወጣቶች በሙሉ እነዛ በጋሸና ምሽግ ጀብድ የሰሩ ፣ ምሽግ የደረመሱ ፣አይበገሬ አናብስት ፋኖዎች እና ያንተው ጀግና ወንድሞች በሃሰት ውንጀላ ፤በአፋኙ መንግስት ታፍነው እና በክህደት ታስረው ነገ ፍ/ቤት ይቀርባሉ ።ስለሆነም ሁሉም ከላይ ጥሪ የተደረገላችሁ ወገኖች በክልሉ ጠቅላይ ፍ /ቤት በመገኘት መስዕዋትነት ለከፈሉ በጀግንነት እና በድል አድራጊነት ከጋሸና ለተመለሱ የቁርጥ ቀን ወንድሞቻችን ፍፁም አብሮነታችን ፤ ጓዳዊ አጋርነታችንን እና አማራዊ ወንድማማችንትን እንድንገልፅ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር የከበረ ጥሪውን ያስተላልፋል ። እንዲሁም ከአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ጋር በግፍ የታሰሩ የአማራ ፋኖ በሸዋ አባላትና አመራሮች ፤የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ አባልና ጋዜጠኛ እና ሌሎች አማራ ወንድሞቻችን በተመሳሳይ የሃሰት ውንጀላ ተይዘዋል ። በመሆኑም ይህን አይን ያወጣ የመንግስት በደል ፥ግፍ ነገ በከልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በመገኘት ለወንድሞቻችን አጋርነታችንን ፣ወንድማማችነትና አብሮነትን እንድንገልፅ በማለት መልዕክታችን እናስተላልፋለን ። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው‼️ ሐምሌ 07/2014 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር

Source: Link to the Post

Leave a Reply