#የፋኖ_መከታዬ‼… «ከወልድያ እስከ ቦሩ ስላሴ…» ዛሬ የማስተዋውቃችሁ ጀግናው ፋኖ አምሣለቃ #ሻበል_ፈቀደ_ያለው ነው፤ አምሳ አለቃ በገባባቸው ውጊያዎች ድል ይቀናዋል! ከልቡ ተዋግቶ ያዋጋል…

#የፋኖ_መከታዬ‼… «ከወልድያ እስከ ቦሩ ስላሴ…» ዛሬ የማስተዋውቃችሁ ጀግናው ፋኖ አምሣለቃ #ሻበል_ፈቀደ_ያለው ነው፤ አምሳ አለቃ በገባባቸው ውጊያዎች ድል ይቀናዋል! ከልቡ ተዋግቶ ያዋጋል! ለአመነበት አላማ ግንባሩን እንጅ ጀርባውን የማይሰጥ ሀሞተ ቆራጥ ቆፍጣና ልበ ሙሉ ነው። አምሳ አለቃ ከጓዶቹ ጋር ነሐሴ3 ቀን2014ዓ/ም ከወልድያ ሲወጡ ከተማዋን ለማሰስ የጁንታውን መንገድ አብሪ አመራር #ገብሬን ጎንደር በር አካባቢ በውሃ ልማት አድርገው ስንወጣ ከተማዋን ጥላት ይዞ ስለነበር ከተማዋን በላድክሮዘር የተጫነውን ኃይል መኪናውን መትተነው ጥለነዉ በስታድዎም ወጥተዋል። አምሳለቃ ወልድያን ከለቀቅን በኋላ ከጓዶቹ ጋር በማደረጀት #በድሬ_ሮቃ ግንባር #አማሮ ላይ ከፍተኛ ውጊያ አድርጎ ምሽግ ሰብሯል። በሐይቅ ግንባር #ሠግለን ላይ በውጊያ ተሳትፎ ትልቅ ድል አምጥቷል፤ በመጨረሻ እኔ በነበርኩበት #በቦሩ_ስላሴ ውጊያ ተሳትፎ ጥላት ወደ ደሴ አዘናግቶ ሊገባ በነበረበት ጊዜ ፋኖ ከፍተኛ ትግል ማድረጉ ይታወቃል፤ በዚህ ግንባር ሆዱ አካባቢ በጥይት በመመታቱ ምክንያት ከባድ ቁስለኛ በመሆን በደሴ ሆስፒታል፤ በባህር ዳር ከፍተኛ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል። ይህ ወንድማችን ለበርካታ ወራት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ቆይቶ በቅርቡ ከባህርዳር ሆስፒታል ወጥቶ ወልድያ መጥቶ ከታናሽ ወንድሙ ላይ ወድቆ እየታመመ ይገኛል። እኔን የገረመኝ ያን ህመሙ ተቋቁሞ በትላንት የፋኖ ምርቃት መገኝቱና ለሰራዊቱ ሞራል መስጠቱ ነው!!! አምሳ አለቃ ትልቅ ሰው ነው ለትግል እስከ ህይወት መስዋትነት እንደሚከፈል ገብቶት ቁሱሉ ሳይደርቅ ምርቃት ላይ ተገኝቶ ህመሙን ችሉ በፅናት ቆሞ «እንኳን ደስአላችሁ!!!» ማለቱ ከሱ የምንማረው ብዙ ነገር እንዳለ አሳይቶናል። ፋኖ እንድህ የአካል! የሞራልና! የህይወት! ዋጋ የሚከፍለው ለአገር ለወገን ብሎ መሆኑን ትረዳለህ!!! ደሴ ከተማ በጥላት የምትያዘው ጥቅምት11 ቀን2014 ዓ/ም ነበር። ደሴ ከቦሩ ስላሴ በሰባት ኪሎሜትር እርቀት ላይ ትገኛለች። ከቦሩ ስላሴ የመጣው ኃይል ደሴን ለሁለት ሰንጥቆ ነበር የሚይዛት፤ አንዱ ኃይል በጢጣ ወርዶ ሐይቅ እና ወረባቦ የገባውን የወገን ጦር ቆርጦ ይይዛል። ሁለተኛው ደግሞ በዳንድቦሩ አቅንቶ በተቋም ዩንቨር_ሲቲውን ዘግቶ ኩታበር እና አላንሻ ሜዳ የገባውን የወገን ጦር ቆርጦ በቀላሉ ይይዝ ነበር!!! በዚያን ወቅቱ የህዝባዊ ሰራዊቱ #ፋኖ #ሚሊሻ #አድማ_ብተና የደሴ ህዝብና ከሰሜን ወሎ ተፈናቅሎ ደሴ የሚገኝው ህዝብ በጭነት ተጭኖ ሀትክክለኛ ህዝባዊ መአበል የተፈጠረበት ቀን ነበር። በተለይ ህዝባዊ ፖሊስ ግን ከማረሳው ልዩ ትውስታዬ ዛሬ ላይ ሳየው ደስ ቢለኝም የዚያኔ ግን ከልብ አስጨንቆኝ የነበረው ወልድያ ያሳደጉኝ አባቶቼ የምላቸው እነ ኮማንደር #ደሳለ_ፀደይ እን ኮማንደር #ደርበውን እነ ኮማደር #ተመስገንን በዚያ ቀውጢ ውጊያ መሀል ሳያቸው አዘንኩ!!! «ለምን እኛ እያለን እነሱ ይሞታሉ???…» አዳር አድረን በማግስቱ በህይወት መኖራቸውን ሳውቅ ደስአለኝ!!! በዚህ ውጊያ ፊት መሪ የነበረው ፋኖ ነበር። በዚህም የተወሰኑ ጓዶች እነ ፋኖ #ሞላ_ደስዬ ሲሰው… እነ አምሳ አለቃ #ሻንበል ደግሞ በከባዱ ቆሰሉ። በመስዋትነት ደሴ በጥላት ሳትደፈር ቆዬች! የወገን ጦር ያላሰበው ያልጠበቀውን ቦታ ቆረጠ በመረዳት ለጊዜውም ቢሆን በነጋታው ማለትም ጥቅምት12 ቀን2014ዓ/ም ከቀኑ 6:30 አካባቢ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቦታው ገብቷል። ለዚህ ነው ፋኖ አለኝታዬ የምለው!!! ክብር ለወገኖቻቸው ነፃነት ሲሉ በዱር በገደል ለተዋደቁት ሁሉ!!! ፋኖ የህዝብ አለኝታ! ፋኖ የህዝብ መከታ!!! በቴዎድሮስ አያሌው (ሀብታሙ) ሚያዚያ፳፰ ቀን፳፻፲፬ዓ/ም ተጣፈ። 28/08/2014ዓ/ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply