
የፋይናስ ደህነት አገልግሎት በመጀመርያ የአማራ 65 ድርጅቶችና ግለስቦች የባንክ አካውንታቸው እንዳይንቀሳቀስ አግዷል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሚያዚያ 28/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የአማራን ህዝብ በኢኮኖሚ የማድቀቅ ፕሮጀክት በአብይ አህመድ አገዛዝ እንደቀጠለ ነው። ሁሉም እንደሚያውቀው የአብይ አህመድ ስርዓት አማራ የሆነን ሁሉ የመንግስት ሰራተኛ፣ ነጋዴ፣ ገበሬ፣ ምሁር፣ ማህበራዊ አንቂ፣ ፖለቲከኛ፣ የፀጥታ ኃይል ሁሉንም የሚያሳድድበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በተለይም አማራን በኢኮኖሚና በፖለቲካ ማዳከም አለብኝ ብሎ የተነሳ የአብይ አህመድ አገዛዝ ቡድን በመጀመሪያ ዙር 37 የአማራ ባለሀብቶችን የትኛውም ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ አግዶ ነበር። ከዛ 45 ባለሀብቶችን አገደ። አሁን ደግሞ ተጨማሪ 21 የአማራ ባለሀብቶችን በማገድ በአጠቃላይ በአቶ አበባው ደስታና ተመስገን ከፍያለው መዝገብ ከ65 በላይ ባለሀብቶች ሀብት ንብረታቸው በአብይ አህመድ የኦሮሙማ አገዛዝ 💯%አማራ በመሆናቸው ብቻ ታግዶባቸዋል። ይህ_ማለት አጠቃላይ የባንክ አካውንታቸው እና ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረታቸው የታገደባቸው 44 ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የባንክ አካውንታቸው ብቻ የታገደባቸው 21 ድርጅቶች እና ግለሰቦች ናቸው በድምሩ 65 ድርጅቶች እና ግለሰቦች የዚህ ስርዓት የግፍ ሰለባ ሆነዋል። በአጭር ቀናት ውስጥ በርካታ ባለሀብቶችን እንደሚያግድይ ይጠበቃል። ወንጀላቸውም 💯% አማራ መሆናቸው ብቻ ነው! ይህ ብቻ አይደለም የአብይ አህመድ የኦሮሙማ አገዛዝ አሁን ደግሞ በየትኛውም ባንክ ከ10ሺ ብር በላይ ያነቃቀሰ አማራ የሆነን ግለሰብ ዝርዝር ላኩልኝ በሚል ለሁሉም ባንኮች ትዕዛዝ ልኳል። ከቀናት በፊት የሸዋ ሰማ የበጎ አደራጎት ማህበር፣ የአማራ ተማሪዎች ማህበርና ሌሎች የበጎ አድርጎት ማህበራት የባንክ አካውንት እንዲፈተሽና እንዲታገድ መደረጉንም አይተናል። የመጣብን ችግር በዚህ የሚያቆም አይደለም። ዋና አላማቸው የአማራን ህዝብ በኢኮኖሚ ማድቀቅ ነው። ይህን ሁሉ በደልና ወንጀል ለማስፈፀም ተባባሪ የሆነው ደግሞ በኢትዮጵያዊነት ካባ ስር ያለው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ነው። ምንጭ-AMN
Source: Link to the Post