የፋይናንስ ተቋማት የብድር አሰጣጥ አሰራራቸውን ግልፅ ለማድረግ አለመፈለጋቸው ለብድር ሂደቱ ችግር እንደሆነ ተሰማ፡፡

የብድር አገልግሎቱን የሚሰጡ የፋይናንስ ተቋማት አሰራራቸውን ለተጠቃሚው ግልፅ ባለማድረጋቸው ተበዳሪዎች ለእንግልት እንደሚዳረጉ ተሰምቷል

የብሄራዊ ባንክ ተወካዩ አቶ በለጠ ፎሎ እንደተናገሩት ብድሩን የሚወስደው ተጠቃሚ አሰራሩን ባለማወቁ ምክንያት በአከፋፈሉ ሂደት ላይ ቅሬታ ያነሳሉ ብለዋል።

ለዚህም ምክንያቱም ባንኮቹም ሆኑ ማይክሮ ፋይናንሶቹ ለተጠቃሚው አካል በቂ መረጃ ለመስጠት አለመፈለጋቸው ነው ብለዋል

በልማት ባንክ ውስጥ ባለሙያ የሆኑት አቶ ይልማ አበበ በበኩላቸው፤ ተበዳሪዎች ብድር እንዲከፍሉ በሚደረጉበት ሂደት ብዙ ቅሬታዎች እንደሚያሰሙ አንስተው፤
ምክንያቱ ደግሞ የፋይናንስ ተቋማት የብድር አሰራራቸውን ግልፅ ለማድረግ ካለመፈለጋቸው የተነሳ እንደሆነ ተናግረዋል።

ባንኮችም ይሁኑ ማይክሮ ፋይናንሶች ብድርን ተቋማዊ ሚስጥር ይመስል አሰራራቸውን እንደሚደብቁ አንስተው ይህንን አስተካክሎ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ ተነስቷል።

የብድር አከፋፈል ስርዓቱ አፅዕኖት ተሰጥቶት ለሚበደረው አካል ሊነገረው እና ሊረዳው እንደሚገባ ተገልጿል።

በለአለም አሰፋ

ሚያዝያ 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply