የፋይዘር ክትባት ከ5 እስከ 11 ዓመት ለሆኑ ልጆች እንዲሰጥ ድጋፍ ቀረበ

https://gdb.voanews.com/85000157-613E-4B47-B6B8-BFFB9F0E6A12_w800_h450.jpg

የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አማካሪዎች ቡድን ሁለቱም የፋይዘር የኮቪድ 19 ክትባት እድሜያቸው ከ5 እሰከ 11 ለሚደርሱ ህጻናት እንዲሰጥ ያለውን ሙሉ ድጋፍ አስታወቀ፡፡ 

ፋይዘር፣ በሰዎች ላይየተደረገው የምርምርሙከራ፣ ክትባቱ እድሜያቸው ከ5 እስከ 11 በሚደርሱ ህጻናት ላይ ኮቪድ-19 የሚያደርሰውን ጥቃት የመከላከል አቅሙ 91 ከመቶ መሆኑን መረጋገጡን አመልክቷል፡፡ 

የምግብና መድሃኒት አስተዳደሩም በዚህ ሳምንት የአማካሪዎቹን ቡድን ሀሳብ ተቀብሎ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ውሳኔው ከጸደቀ 28ሚሊዮን አሜሪካውያን የክትባቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ እንደሚሆኑ ተገምቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply