የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የዐቃቢ ህግ የይግባኝ አቤቱታ ያስቀርባል በማለት ለነገ ህዳር 20/2015ዓም 3፡00 ላይ እንዲቀርቡ ሲል ትዕዛዝ በመስጠት ቀጠሮ ይዟል! ሕዳር 19 ቀን 2015 ዓ….

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የዐቃቢ ህግ የይግባኝ አቤቱታ ያስቀርባል በማለት ለነገ ህዳር 20/2015ዓም 3፡00 ላይ እንዲቀርቡ ሲል ትዕዛዝ በመስጠት ቀጠሮ ይዟል! ሕዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የካቲት 03 /2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ከ35 ተከሣሾች መካከል 4ቱን ነጻ ብሎ በማሰናበት በሌሎቹ 31 ተከሣሾች ላይ ደግም ከ16 ዓመት እስከ 25 ዓመት የቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ አይዘነጋም። በመሆኑም 1. ኮርኔል ፈንታሁን ሙሀባው፣ 2. ኮርኔል ሞገሥ ዘገዬ፣ 3. ታጋይ ስለሺ ከበደ እና 4. አቶ ይማነ ታደሰ የአብክመ ሠላምና ደህንነት የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የነበሩትን ጨምሮ በሁለቱ መዝገብ ያሉ ሌሎችም ፍ/ቤት ይቀርባሉ። ጉዳያቸው የሚቀርበውም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2ኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን ፍ/ቤት የሚቀርቡትም:_ 1ኛ የኮ/መ/ቁ 224852 ይግባኝ ባይ:- የአብክመ ዐ/ህግ መልስ ሰጭ:-እነ የማነ ታደሰ 35 ሰዎች 2ኛ የኮ/መ/ቁ 211179 ይግባኝ ባይ:- የአብክመ ዐ/ህግ መልስ ሰጭ:- እነ ሻለቃ ሹመት የሱፍ (19 ሰዎች) ነገ ህዳር 20/2015ዓም 3፡00 ላይ የሰኔ 15ቱ የጦር መኮነኖች ይግባኝ ክሱ ያስቀርበል በሚል በነፃ የተስናበቱም ሆነ እድሜልክ የተፈርደባቸውም ፍርደኞችም እንዲቀርቡ ትዕዛዝ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀጥሯል። እነ አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ የክስ ፋይላቸው የተዘጋ ተከሳሾችም እንዳሉ ተገልጿል። ከሰኔ 15ቱ የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አርበኛ ዘመነ ካሴን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች የይግባኝ መልስ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰምቷል በቅርቡ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለው ሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ (55 ሰዎች) በተከሰሱበት መዝገብ 14ኛ ተከሳሽ የነበረው ወንድማችን ዘመነ ካሴ በሌለበት በተደረገው ክርክር ከሌሎች 16 ተከሳሾች ጋር በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 141 መሰረት መከላከል አያስፈልገውም ተብሎ በነፃ የተለቀቀው በ2013 ዓ.ም ነበር። ትዕዛዙ ሊመጣ “የሚችለው” መልስ ሰጭወች ነፃ መለቀቃቸውን ተከትሎ የክልሉ ዐቃቤ ሕግ በተሰጠው ውሳኔ ባለመስማማት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ ካቀረበ እና ፍርድ ቤቱም ይግባኝ የተጠየቀባቸው ግለሰቦች ለይግባኙ መልስ መስጠት እንዳለባቸው ሲያምን ነው ። ሁሉም አማራ ለፍትህ ድምፅ እንድትሆኑ እንጠይቃለን።!! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply