የፌደራልና የክልል ም/ቤት የህዝብ ተወካዮች ከባህር ዳር ዙሪያ እና ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ ጋር ውይይት አካሄዱ። ባህርዳር:- የካቲት 28/2014 ዓ.ም…

የፌደራልና የክልል ም/ቤት የህዝብ ተወካዮች ከባህር ዳር ዙሪያ እና ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብ ጋር ውይይት አካሄዱ። ባህርዳር:- የካቲት 28/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የፌደራልና የክልል የህዝብ ተወካዮች በመልካም አስተዳደር ፣በመሰረተ ልማት ፣በማህበራዊ ልማት እንዲሁም በጸጥታ ዙሪያ ከባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ እና ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማኅበረሰብ የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በጢስ አባይ ከተማ ውይይት አካሄደዋል፡፡ በውይይቱ ተሳታፊዎች የመልካም አስተዳደር ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ከባህርዳር ዙሪያ ወረዳ እና ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር በተውጣጡ የማህበረሰቡ ክፍሎች ጋር ውይይት ተካሄዷል፡፡ በመድረኩ አወያይ የነበሩ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የፌደራልና የክልል ም/ቤት ፣ህዝብ ተወካዮች እንዲሁም የባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ም/አፈ ጉባኤ በመሆን ውይይቱን መርተዋል፡፡ አወያዮችም በማህበረሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ለሚመለከተው አካል በማድረስ መፍትሄ ለማሰጠት ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡ ሙሉ ዝግጂቱን ከደቂቃዎች በኋላ በአሻራ ዩትዩብ ቻናል ይጠብቁን ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply