
የኢትዮጵያ ፌደራል ሠራዊት እስከ መጪው ሐሙስ ድረስ ወደ ትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ በመግባት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጀምር ተነገረ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና ከህወሓት ሪዎች ጋር የተደረገውን ድርድር መንግሥትን በመወከል በመሪነት የተሳተፉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንዳሉት ሠራዊቱ በዚህ ሳምንት ወደ መቀለ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
Source: Link to the Post