የፌደራል መንግሥትን እና በህወሓት የሚገኙ ወንጀለኞችን ለማሸማገል ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል ተብሎ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ዜና ሀሰት መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወ…

የፌደራል መንግሥትን እና በህወሓት የሚገኙ ወንጀለኞችን ለማሸማገል ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል ተብሎ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ዜና ሀሰት መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወ…

የፌደራል መንግሥትን እና በህወሓት የሚገኙ ወንጀለኞችን ለማሸማገል ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል ተብሎ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ዜና ሀሰት መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኀብረት ሊቀ መንበር የሆኑትን የሲሪል ራማፎሳን ልዑካን ተቀብለው በግል እንደሚወያዩ ተገልጧል። ሆኖም፣ የፌደራል መንግሥትን እና በህወሓት የሚገኙ ወንጀለኞችን ለማሸማገል ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል ተብሎ በመሰራጨት ላይ የሚገኘው ዜና ሀሰት መሆኑን እናረጋግጣለን ብሏል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመግለጫው። ድርድርን አስመልክቶ የፌደራል መንግሥት ያለው አቋም ፈጽሞ ያልተለወጠ ነው ብሏል። በተመሳሳይ ዛሬ ኅዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲግራት ከሕወሓት ጁንታ ነጻ ስለመውጣቷ ተገልጧል። ይህን ተከትሎም አሲምባ የእንኳን ደስ አላችሁ በማለት የኢሮብ ህዝብ የራስ አስተዳደር እንዲመሰረት ጠይቋል። የመከላከያ ሠራዊቱ በትናንትናው እለት አክሱምንና አድዋን መቆጣጠሩን በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወሳል። ዛሬው እለትም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ መቀሌ እያመራ ነው ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply