የፌደራል መንግስትና የህወሃት አመራሮች የናይሮቢውይይት ዛሬም ይቀጥላል፤በአፍሪካ ኅብረት አስተባባሪነት የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች ሰኞ'ለት ናይሮቢ ላይ የጀመሩት ውይይ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/lZnfDAStY4rMDabSyEWqvtvwEmNFz9ygNEZKYyjYfN821aw-HIP0c2dFbmOnaw92qwNnkhaCBe5wqQoLxrtLfWzs_xibVyzo5PKKxI9Sb9GokxJiCbnay3JbijZO3rQxf-ikJaqenkuH9tIqgsIEz9BY8hnuhVu8auKvBxtg6GU6mU4nNE-fQEhUOqLI75JZMuQk8iwYpvcp2nzfHjla1b-nUjKUNUVaTA9L7aZThNjJpORnEZaY-BKptqeHvFYc7afr89JyICbpnhLxzdJp8ErMbKC3W50ECzpGMnltalzOPQ0oedAIw_UPeBmV6ptH9A70vNnLrnBeVDvsiX3xYA.jpg

የፌደራል መንግስትና የህወሃት አመራሮች የናይሮቢውይይት ዛሬም ይቀጥላል፤

በአፍሪካ ኅብረት አስተባባሪነት የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች ሰኞ’ለት ናይሮቢ ላይ የጀመሩት ውይይት ዛሬም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
አሶሴትድ ፕሬስ ዛሬ የውይይቱ መጠናቀቂያ እንደሚሆን ዘግቦ ነበር።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረጉት ውይይቶች ምን አወንታዊ ውጤት እንደተገኘ አፍሪካ ኅብረት ያለው ነገር የለም።
በውይይቱ የሁለቱ ወገኖች ሲቪል ተወካዮችም ተሳታፊ ናቸው ተብሏል።

የቪኦኤ ዘገባ እንደሚያመለክተዉ ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ በናይሮቢ የቀጠለውን የሠላም ሥምምነቱን ሂደት እደግፋለሁ ብላለች፡፡
በሰላም ስምምነቱ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የአማራ አፋርና ትግራይ አካባቢዎች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ማድረስና አገልግሎቶችን ወደነበሩበት መመለስ የሚል መካተቱን ተረድተናል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ፤ አሜሪካ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሂደትን ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በመሆን አሜሪካ ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች ብለዋል።
ለዚህም ተግባራዊነት የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ በስፍራው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሥምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ ናይሮቢ ውስጥ በማካሄድ ላይ የሚገኙትን ውይይትም እንደምትደግፈው ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
አያይዘውም ሁለቱም ወገኖች የጦር መሳሪያ ድምጾችን ዝም ለማሰኘት ቁርጠኝነታቸውን የሚያሳይ ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply