የፌደራል መንግስት እና ህወሃት የፖለቲካ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ።በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የፌደራል መንግስት ልኡክ ዛሬ መቀሌ ገብቷል።ልኡኩ መቀሌ አሉላ አባነጋ…

የፌደራል መንግስት እና ህወሃት የፖለቲካ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ።

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የፌደራል መንግስት ልኡክ ዛሬ መቀሌ ገብቷል።

ልኡኩ መቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ፣ የህውሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አቀባበል አድርገውለታል።

የመከላከያ እና የትራንስፖርትና ሊጂስቲክ ሚኒስትሮችን ያካተተው የፌደራል መንግስት ልኡክ፣ ከህወሃት እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ምክክር ማድረግ ጀምረዋል ነው የተባለው።

የፌደራል መንግስቱ እና ህወሃት የሁለት አመቱን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለመቋጨት፣ በፕሪቶሪያ በደረሱት ስምምነት መሰረት፣ በፍጥነት ፖለቲካዊ ውይይት መጀመር ቢኖርባቸውም በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይቷል።

ሁለቱም ወገኖች በመቀሌ ምክክር ሲጀምሩ የፖለቲካዊ ንግግሩ በመደበኛነት እንዲቀጥል መስማማታቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጥር ወር መጨረሻ ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ፣ ከህወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ፊት ለፊት መገናኘታቸው ይታወሳል።

በዚህ ምክክርም ሁለቱም አካላት የፖለቲካ ውይይት ለመጀመር መስማማታቸው አይዘነጋም።

መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply