የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ በጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ጎበዜ ሲሳይ ላይ ክስ የመመስረቻ ተጨማሪ ቀናት “ለመጨረሻ ጊዜ” ፈቀደ  

በተስፋለም ወልደየስ

የፌደራል ዐቃቤ ህግ፤ በጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ጎበዜ ሲሳይ ላይ ክስ የሚመሰርትበት ተጨማሪ አራት ቀናት በፍርድ ቤት ተፈቀደለት። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ቀናቱን የፈቀደው “ለመጨረሻ ጊዜ” መሆኑን ዛሬ ሰኞ መስከረም 16፤ 2015 በዋለው ችሎት አስታውቋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው፤ በዐቃቤ ህግ የቀረበለትን አቤቱታ በቢሮ በኩል ከተመለከተ በኋላ ነው። ዐቃቤ ህግ ለችሎቱ በጹሁፍ ባስገባው በዚሁ አቤቱታ፤ በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ሲካሄድ የቆየውን የምርመራ መዝገብ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መምሪያ ከተቀበለ በኋላ፤ ክስ ለመመስረት የሚያስችለው 15 ቀናት እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቆ እንደነበር አስታውሷል። 

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ መስከረም 11 በዋለው ችሎት ግን ክስ ለመመስረቻ የተሰጡት አምስት ቀናት ብቻ እንደነበር ጠቅሷል። ከእነዚህ ቀናት ውስጥ የመንግስት የስራ ቀናት “ሁለት ብቻ” እንደሆኑ ለፍርድ ቤቱ ያስረዳው ዐቃቤ ህግ፤ እነዚህ ቀናት አጭር በመሆናቸው “በምርመራ መዝገቡ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በቂ ጊዜ አላገኘንም” ብሏል። በዚህም ምክንያት ክስ ለመመስረቻ ተጨማሪ 10 ቀናት እንዲሰጡት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) 

[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይታከሉበታል]

The post የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ በጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ጎበዜ ሲሳይ ላይ ክስ የመመስረቻ ተጨማሪ ቀናት “ለመጨረሻ ጊዜ” ፈቀደ   appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply