የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ30 ሺህ ብር ዋስትና “ዛሬውኑ ከእስር እንዲለቀቅ” ትዕዛዝ ሰጠ

በሃሚድ አወል

የ“ፍትሕ” መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት ተፈቀደለት። ለጋዜጠኛ ተመስገን ዋስትናውን የፈቀደው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት፤ ተመስገን ደሳለኝ “ዛሬውኑ ከእስር ይለቀቅ” ሲል ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ በነበረው የችሎት ውሎ ጋዜጠኛ ተመስገን፤ ከዚህ በፊት ለዋስትና ያስያዘው 100 ሺህ ብር አሁን ከተፈቀደለት ዋስትና ተቀንሶ ተመላሽ እንዲሆን አዝዟል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 27፤ 2014 ባስቻለው ችሎት ለጋዜጠኛ ተመስገን የመቶ ሺህ ብር ዋስትና ፈቅዶ ነበር። 

በዚህ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር የተሰኘው የፌደራል ዐቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለቱ፤ ለጋዜጠኛው የተፈቀደው ዋስትና ታግዶ ተመስገን ያለፉትን አራት ወራት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አሳልፏል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

The post የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ30 ሺህ ብር ዋስትና “ዛሬውኑ ከእስር እንዲለቀቅ” ትዕዛዝ ሰጠ appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply