You are currently viewing የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ችሎት በታሪክ ተመራማሪው ጋሽ ታዲዎስ ታንቱ የመከላከያ ምስክር አሰማም ሂደት ላይ በዳኞች ልዩነት ለብይን ትዕዛዝ ሰጥቷል።      አማራ ሚዲያ ማዕ…

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ችሎት በታሪክ ተመራማሪው ጋሽ ታዲዎስ ታንቱ የመከላከያ ምስክር አሰማም ሂደት ላይ በዳኞች ልዩነት ለብይን ትዕዛዝ ሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕ…

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ችሎት በታሪክ ተመራማሪው ጋሽ ታዲዎስ ታንቱ የመከላከያ ምስክር አሰማም ሂደት ላይ በዳኞች ልዩነት ለብይን ትዕዛዝ ሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 17/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በመከላኪያ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች የኦሮሞ ብሄር ስብጥር እና አደረጃጀት አስመልክቶ እንዳይመሰክር ዐቃቢ ህግ ተቃውሟል። ይኽ አግባብ አይደለም ጠሚሩ በምክር ቤት ቅፅል ስም እየጠሩ ቀበሮ፣ አንበሳ፣ ነጓድጓድ ሲሉ ነበር ጋዜጠኛዉ ሙያዊ የጋዜጠኝነት ምርመራ የደረሱበትን ድምዳሜ እና በተከሳሽ ከቀረበው ክስ ተነስተን ነው ምስክሩ ቃላቸውን የሚሰጡት ብለዋል ጠበቆች። የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ችሎት በአንደኛ ተከሳሽ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ የመከላኪያ ምስክር አሰማም ሂደት ዛሬ ሐምሌ 17/2015 ዓ,ም በነበረው ቀጠሮ የተከሳሽ መከላኪያ 2ኛ ምስክር በህመም ምክንያት ሊገኙ አልቻሉም 6ኛ 7,8,9 እንዲሁም 13ኛ እና 15ኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ በመሆናቸው በሌላ ሰዎች እንዲቀየሩ ትህዛዝ እንዲሰጥ ጠበቆች ጠይቀዋል። 12ኛ የተከሳሽ ምስክር በዛሬው ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተገኝቷል። ቃለማህላ ከፈጸሙ በኃላ በማለት የምስክር ጭብጥ ጠበቃ ታለማ ግዛቸውና አዲሱ ጌታነህ የቀረበ ሲሆን በዋናነት በመከላኪያ ሠራዊት አመራር የብሄር ስብጥር ምን እንደሚመስል እና ከጋዜጠኝነች የምርመራ ሙያ ጋር በማያያዝ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ በመጽሔትና ጋዜጦች ያሳተሟቸው ጹሑፎች እንዲያብራሩ ለፍርድ ቤቱ ጠበቆች ቀርቧል። ዐቃቢ ህግ የተከሳሽ ምስክር የኦሮሞ ብሄር ይበዛል አደረጃጀቱን አስመልክቶ ለመግለጽ ሙያዊ ማለት ምን ማለት ነው? የመከላኪያ ሙያ ያላቸው ኤክስፐርት ናቸው ወይ? ጋዜጠኛ ከሆኑ የመከላኪያ የተቋሙን አደረጃጀትና የብሄር ስብጥር በምን ሁኔታ እና እንዴት ሊያቀርቡ ይችላሉ? ስለዚህ ምስክሩ ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በክሱ ላይ የብሄር አደረጃጀት የሚል የለም በምን አግባብ መመስከር ይችላሉ? ስለዚህ ያሰናብትልን በማለት ተከራክረዋል በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ ምስክሩን ከተቀበለ የመከላኪያ አመራርና እንዲሁም አደረጃጀት የሀገሪቱ ከፍተኛ ሚስጥር የደህንነት ጉዳይ ስለሆነ በዝግ ችሎት መታየት አለበት ሲሉ ገልጸዋል። ጠበቆቹም መልስ የተሰጠ ሲሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከምርመራ ጋዜጠኝነት ተነስቶ የደረሰበት ጥናት እንዲሁም በጉዳዩ ላይም ተከሰዉበት በነጻ የተሰናበቱ በመሆናቸው የጋዜጠኝነት ምርመራ ሙያዊ ሃላፊነት በመሆኑ ይህን መመስከር ይችላሉ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ውድቅ ሊያደርገው ይገባል ብለዋል። በሌላ በኩል በክሱ ላይ የብሄር ስብጥር እና አደረጃጀት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን ላይ ማየት ይችላል ዐቃቢ ህግ ክሱን አያዉቁትም ማለት ነው። የመከላኪያ አደረጃጀት በአዋጅ ተጠቅሶ በክሳቸው ላይ ቀርቧል በዚህ አግባብ ምስክሩ እንዲመሰክሩ ይደረግ በዝግ ችሎት ይሁን ማለት ትክክል አይደለም የተከሳሹን በህግ የመዳኘት መብት የሚጋፋ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም ሲሉ አክለዋል። መከላኪያ ከህግ በላይ አይደለም ለፍርድ ቤቱ የሚደበቅ ሚስጥር የለም በህግ በፊት ሚስጥር የለም ማስረጃ ታይቶ ነው ውሳኔ የሚሰጠው መከላኪያ ውስጥ የሚሰሩ አመራርች ጠሚሩ ሳይቀር በቅፅል ስማቸው ፥ቀበሮ ፥አነፍናፊ አንበሳ እያሉ ሲጠሯቸው ነበር በአደባይ የሚታወቁ ሃላፊዎች ናቸው ስለዚህ ሚስጥር አይደለም ፍርድ ቤቱ ምስክር አሰማም ሂደቱ እንዲቀጥል ይደረግ በማለት ጠበቆች በአጽኖት ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ከተወያየበት በኃላ ሁለት ዳኞች በልዩነት አቋም በመያዛቸው ያለመስማማት በልዩነት ተለያይተዉ የመሀል ዳኛው ባሉበት በድጋሚ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ጠይቀዋል። በዚህም 12ኛ የተከሳሽ መከላኪያ ምስክር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አሰማም ሂደት መመስከር ይችላሉ ወይስ ተቀባይነት የለውም ለማለት እንዲሁም ባልተገኙት የመከላኪያ ምስክሮች ሌላ ሰዎች ለማቅረብ ትህዛዝ እንዲሰጥበት በ18ኛ ላይ የተጠቀሱት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጹሑፍ መልስ በድጋሚ ፍርድ ቤቱ ትህዛዝ ለማውጣት በእንግሊዘኛ የተተረጎሙ መጽሐፍቶች ተከሳሹ አይተዋቸው መልስ ለመስጠት ለሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱ ተጠናቋል። ፅናት ሚዲያ የችሎት ዘገባ_ስንታየሁ ቸኮል

Source: Link to the Post

Leave a Reply