የፌደራል ፍርድ ቤቶችና የተረኞች ወረራ አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 14/2013 ዓ.ም ባህር ዳር የፈደራል ፍርድ ቤቶች በተረኞች የኦሮሞ ተወላጆች የተዋቀረ ስለመ…

የፌደራል ፍርድ ቤቶችና የተረኞች ወረራ አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 14/2013 ዓ.ም ባህር ዳር የፈደራል ፍርድ ቤቶች በተረኞች የኦሮሞ ተወላጆች የተዋቀረ ስለመኖሁ ከአሁን በፊት ከየ አቅጣጫው አስተያየትና ጥቆማ ሲሰነዘር እንደነበር የሚታወስ ነው ፡፡ ዛሬ ደግሞ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማለትም የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አራጊ ፈጣሪዎች ኦሮሞዎች ስለመሆናቸው ለአሻራ ሚዲያ መረጃ ደርሶታል እንደሚከተለው ነው፡፡… ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮች ቀጥሎ በተለያዩ ክፍሎች ወደ እናንተ የምናደርሰው የፌደራል ፍርድ ቤቶችን የሚመለከት መረጃ የጸሀፊው ወይም የምንጫችን እንጅ የአሻራ ሚዲያ አቋም እንዳልሆነ እንድትገነዘቡልን እንጠይቃለን፡፡ ክፍል አንድ(1) የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን በተመለከተ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ራሱን የቻለ የመንግስታዊ ተቋም ሲሆን ኃላፊነቱም የዳኞች ነፃነት እና ተጠያቂነት የተባሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ የሆኑ የነፃ ዳኝነት ማንበሪያ ምሶሶዎች ሳይዛነፉ ለማስኬድ የተቋቀመ ራሱን የቻለ የፍርድ ቤቱ አስተዳደር አካል ነው፡፡ ይህ ጉባኤ የዳኞችን ሹመት፣ ዝውውር፣ ደመወዝ (ጥቅማ ጥቅም) እና የዲሲፕሊን ጉዳይ የመወሠን ስልጣን አለው፡፡ ልክ ለአስፈፃሚው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ሁሉ፤ለፍርድ ቤቱ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ብለን በቀላሉ ልናመሳስለው እንችላለን፡፡ ወዲህ ግን ስልጣኑ ከፍ ይላል፡፡ በአውሮፖ ህብረት የዳኞች ጉባኤ ትስስር ኮሚቴ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን ለፍርድ ቤቶች reform የማይተካ ሚና እንዳለው፤ፍርድ ቤቶች በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መመራት እንዳለባችው ያስገነዝባል፡፡ በኢትዮጵያም ነፃ ዳኝነት ለማቋቋም አስፈላጊነቱ ታምኖበት በህገመንግስቱ ውስጥ በአንቀጽ 78 እና 79 ላይ እውቅና ተሠጥቶታል፡፡ ህገመንግስቱ ጥቅል ህግ በመሆኑም ራሱን ችሎ አዋጅ ቁጥር 684/2002 መሠረት የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በዝርዝር ተቋቁሟል፡፡ በአዋጁ መግቢያ ላይም “ነፃ የዳኝነት አካል ነፃነቱ የሚረጋገጠው ተቀማዊ እና ዳኝነታዊ ነፃነቱን መጠበቅ ሲቻል በመሆኑ፤ ይህንንም ለማድረግ ፍርድ ቤቶች ከማናቸውም አካል ተጽዕኖ ነፃ ሆነው ራሳቸውን ማስተዳደር መቻል ያለባቸው በመሆኑ” ሳቢያ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የተቋቀመ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ የጉባኤው አባላት ስብጥር እነማን መሆን እንዳለባቸው በአዋጁ አንቀጽ 5 ላይ ሠፍሯል፡፡ የጉባኤው ሰብሳቢም የጠ/ፍ/ቤቱ ፕሬዜዳንቷ እንዲሆኑ ይደነግጋል፡፡ ከሌሎች የተወካዮች ምክር ቤት፣ አስፈፃሚው አካል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሚመጡት ተወካዮች ውጭ ከፍርድ ቤቱ የሚወከሉት በጉባኤው የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንቶች፣ የከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ብሎም ከዳኞች የተወከሉ አንድ ዳኛ እንደሆነ ሠፍሯል፡፡ ከላይ የተመለከተው የህጉ ሃሳብ ሲሆን በዚህ በህግ እውቅና ተሰጦት ፍርድ ቤቱን በሚመራው ትልቅ ተቋም ላይ “regional and cultural inclusiveness” መኖር እንዳለበት በተለይም እንደኛ ሃገር power sharing arrangement በሚከተሉ አገራት ህገመንግስት ከዲሞክራሲያዊነት መርሆች መካከል አካታችነት እና አሳታፊነት (inclusiveness and participatory) ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው በብዙ የፖለቲካም ሆነ የህግ ሊህቃን ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡ ማንኛውም የዳኛ አመራር (ዳኛ) ህዝብን ማገልገል ያለበት ያለአድሎ ሁሉንም ህዝብ በእኩልነት መሆኑ የሚስተባበል አይደለም፡፡ ነገር ግን አንድ ህዝብ ለተቋማቱ እኩል ተሳትፎ እንደማንኛውም ብሄር ሊኖረው ይገባል፡፡ በተቋሙ ያለው ተሳትፎ ተመጣጣኝነት እንደተባለው ብቻውን ራሱን ችሎ መሠረታዊ የዲሞክራሲ መርህ ሆኖ ስለሚቆም፡፡ በዚህ ረገድ በፌዴራሉ ፍርድ ቤት በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ከዳኞችና ከአመራሩ የተወከሉትን እንደሚከተለው ሠፍሯል፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ (ኦሮሞ) የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት … አቶ ሰሎሞን አረዳ (ኦሮሞ) የፌዴራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … አቶ ብርሃነ መስቀል ዋጋሪ (ኦሮሞ) የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … አቶ ፎአድ ኪያር (ትግሬ) የፌዴራል ዳኞች የተወከለ … አቶ ተኽሊት ይመስል (ትግሬ) የዳኞተ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ … አቶ ዘሪሁን ጌታሁን (ኦሮሞ) ሲሆኑ፣ በተራ ቁጥር 5 ላይ የዳኛ ተወካይ ሆነው የሚገቡት ዳኛ በትንሹ ላለፉት 8 ዓመታት ያገለገሉ፣ በቀድሞው ስርዓት ታማኝነታቸው ተወካይ የነበሩ አና አሁን ደግሞ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙ በመሆናቸው በህጉ መሠረት ከሄድን አንድ ዳኛ ወደ አመራርነት ከተሻገረ፤ የዳኛ ተወካይ ሆኖ ጉባኤው ለይ መሳተፍ የለበትም፡፡ በመሆኑም የተገለጹት አመራር በጉባኤው የዳኛ ተወካይ ሆነው መግባት የሌለባቸው ናቸው፡፡ አሁንም ቢሆን በእሳቸው ላይ የዳኛ ተወካይ ሊሆኑ አይችሉም በሚል እየገፋ በመጣው የዳኞች ጥያቄ መሠረት የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት ከራሳቸው ብሔር የመጣን ዳኛ ተወካይ እንዲሆን የሚቀርቦቸውን የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ለምርጫ እያግባቡ /lobby እያደረጉ/መሆኑ የሚሠማ ነው፡፡እዚህ ላይ ተወካይነታቸው ለዳኞች እንጂ ለአመራሩ አለመሆኑ አጽንኦት መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የዳኞችን ሹመት፣ ጥቅማጥቅም፣ ዝውውር እና ዲሲፕሊን የሚመለከተው፤ነፃ ዳኝነት የሚያስረግጠው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ስብጥር ምን ያክል ከስረ መሰረቱ የሌላ ብሔር ተዋጽኦ አግላይና ገፊ መሆኑን ከላይ የተገለጸው ዝርዝር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ከላይ ያየነው አንኮር ነጥብ እንደተጠበቀ ሆኖ ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተመለከቱት የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ዓባላት የሆኑ አመራሮች በሖላም እንደምንመለከተው የፍርድ ቤት ማኔጅመንት ካውንስል አባላት መሆናቸውን ላጤነ፤ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ፍርድ ቤቱን እንዲመራ በህግ የተቆቆመ /dejure/ ተቆም ቢሆንም በመሬት ላይ /defacto/ አራጊ ፈጣሪዎች ግን የማኔጅመንት ካውንስሉ አባላት ናችው፡፡የማኔጅመንት ካውንስሉ አባላት ደግሞ ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንቷ/ቶች/ ነው፡፡ እንዲያውም የፍርድ ቤቱን አመራር ተመልክተን ዳኞች የምንለው ቀልድ መሰል ነገር አለ፤ ይህዉም ፍርድ ቤቱ የህዝብ እና የመንግስት መሆኑ ቀርቶ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሁኖል የሚል ነው፡፡ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ እና የፍርድ ቤቱ ማኔጅመንት ተመሳሳይ የአባላት ስብጥር ስላሉት checking mechanism አይኖርም፡፡ በተጨባጭ አሁን በመሬት ላይ ያለው፤ በግሃድ የሚታወቀው ውሳኔ የሚሰጡት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ም/ፕሬዚዳንት፣ የከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እና የዳኞች አስተዳደር ጉበኤው ኀላፊ በጋራ ሲሆን ሌሎች አባላት ለይስሙላ የተቀመጡ ናቸው በሚል በዳኞች ይነገራል፡፡ ዳኞች ህገ-መንግስቱ ነጻ ዳኝነት ጽንሰ ሃሳብ በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ኀላፊነት ላይ ያኖረ መሆኑን ቢያሰፍርም የህገ-መንግስቱ መንፈስና ተግባሩ ግን ለየቅል ነው፡፡እዚው በዚያውም በብሄርተኝነት ስሜት ሽፋን በጥቅም የተሳሰረ ቡድን ያለ መሆኑን መረዳት ያሻል፡፡ የፍርድ ቤት ማኔጅመንት ካውንስል በተመለከተ የፍርድ ቤተ ማኔጅመንቱን በተመለከተ የፍርድ ቤቱን አሠራር የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ካለው ኃላፊነት በመለስ ያለው ድርሻ ተቀብሎ የሚያስተዳድር አካል ነው፡፡ የድጋፍ ሠጭዎችን ሹመት፣ ቅጥር፣ እድገት እና ዝውውር የሚመለከት ሲሆን የፍርድ ቤቶችን የየራሳቸውም ሆነ በወል የሚያደረጉትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴና ግዥ የሚመራ ነው፡፡ ይህ የፍርድ ቤት ማኔጅመንት ልክ ከላይ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ላይ አካታችና አሳታፊ መሆን አለበት ብለን እንዳየነው፤ ፍሬ ሃሳቡን ለዚህም የምንዋሰው ይሆናል፡፡ ስብጥራቸውም እንደሚከተለው ሠፍሯል፡- 1.1. የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ /ኦሮሞ/ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት … አቶ ሰሎሞን አረዳ /ኦሮሞ/ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኀላፊ…..አቶ ቦጃ ታደሰ/ኦሮሞ/ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉበኤ ጽ/ቤት ኀላፊ….አቶ ዘሪሁን ጌታሁን/ኦሮሞ/ 2.1. የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … አቶ ብርሃነመስቀል ዋጋሪ /ኦሮሞ/ የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት …. አቶ ተኽሊት ይመስል /ትግሬ/ የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት… ወ/ሮ ተናኘ ጥላሁነ (አማራ)?? የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት … አቶ ፉአድ ኪያር /ትግሬ/ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት …. አቶ ተስፋየ ንዋይ /ኦሮሞ/ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት …. ወ/ሮ አሸነፈች አበበ /ደቡብ/ ከላይ በፍርድ ቤቱ የማኔጅመንት አመራር ስብጥር ላይ ከአማራ የተወከሉት በፌዴራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት በምክትል ፕሬዘዳንትነት የተመለከቱት አመራር ብቻ ናቸው፡፡ በህገመንግስቱ አንቀጽ 78(2) ላይ እንደተመለከተው የፌዴራሉ መንግስት ከፍተኛ የዳኝነት አካል የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከመሆኑ አኳያ የሳቸው ሹመት እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው እንዲሉ፤እንዴያው በጥቅሉ ሚና የሌለው እዚህ ግባ የማይባል ሹመት ነው፡፡ ነገሩን ነው እንጅ ለአማራ ብሔር ማን ተወካይ እንደሚመረጥለት ድሮም ሆነ አሁን ግራ የሚያጋባ ቢሆንም፤ እዚህ ላይ ተያያዥ የሆነ ነገር ላንሳ ከለውጡ በፊት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ከሹመቱ በፊት ራሳቸውን የሚጠሩትም ሆነ የመስሪያ ቤት ግል ማህደራቸው የመጡበት ብሔር ሌላ የነበረ በወቅቱ የነበሩት አስፈፃሚዎች ፊት ታማኝነታቸው ከፍ ያለ በመሆኑ ብሔራቸውን ወደ አማራ ተለውጦ በአማራ ብሔር ስም የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ፕሬዚዳንት ሁነው ተሾሙ ተብሎ ይነገር ነበር፤ ቅሉ የአሁኗ ተሿሚ ሁኔታም ከዚያ ባይዘልም፡፡ (የመጀመሪያውን አባሪን ይመለከቷል፡፡ በነገራችን ላይ የተየያዘው ማስረጃን ከክፍለ ከተማው ማረጋገጥ ይቻላል፤ በፍርድ ቤቱ በሚሞላ ኢንሹራንስ ወረቀት ላይ ብሄር ኦሮሞ በሚል ፕሬዘዳንቶ የሞሉ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡) ወደ አነሳነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ም/ፕሬዚዳንት ነጥብ ስንመለስ አመራሯ በቤተሰባዊም ሆነ ስነልቦናዊ ሁኔታቸው የአማራ ተወካይ ለመሆን የሚቸግራቸው ባሉበት የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት ተጽዕኖቸው እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ላጤነ ደግሞ በፍርድ ቤቱ ማኔጅመንት ላይ አንድም የአማራ ብሔር ተሳትፎ የለውም ብሎ ደፍሮ ለመናገር ይዳዳል፡፡ የጠቅላይ ፍ/ቤት የዳኞች ስብጥር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 78/2/ ላይ በግልጽ እንደተደነገገው የፌዴራሉ መንግስት ከፍተኛ የዳኝነት አካል የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንደሆነ፤ የዚህ ተቋም የበላይ አመራሮች ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት እንደሆኑ፤ ሹመታቸውም ከሌሎች የከፍተኛው እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶችና ዳኞች በተለየ ሁኔታ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾሙ በአንቀጽ 81(1) ላይ ተደንግጓል፡፡ ህገመንግስቱ ጠቅላይ ፍ/ቤቱን ከፍተኛ የዳኝነት አካል መሆኑን ከመግለጽ አኳያ በዚህ ፍርድ ቤት የአመራሩንና የዳኞች ስብጥርን መመልከት አስፈላጊ ነው፡፡ በነገራችን ላይ በህገመንግስቱ አንቀጽ 80/3//ሀ/ ላይ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት መሠረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበትን ማናቸውም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሠበር ችሎት የማየት ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ይህንኑ ለማብራራት በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሠረት በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሠየሙበት የሠበር ችሎት የሚሠጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኝ የፌዴራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት እንደሚኖረው ተደንግጓል፡፡ ይህንን አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሚሠጠው የሠበር ችሎት የዳኞች የብሔር ስብጥር ስንመለከት 1ኛ ሰበር ችሎት ከ5ቱ ዳኞች 4ቱ/ኦሮሞ/፤ 2ኛ ሰበር ችሎት ከ5ቱ ዳኞች 3ቱ/ኦሮሞ/፤3ኛ ሰበር ችሎት ከአምስቱ ዳኞች 3ቱ/ኦሮሞ/ ናቸው፡፡ ሌላው High profile criminal cases /የወንጀል ጉዳዮችን/ የሚያዩት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁልቱ ችሎቶች ውስጥ /መካከል/ ከሶስት ዳኞች በሁለቱም እያንዳዱ ችሎት ስብጥር ላይ ሁለቱ /በድምሩ ከ6ቱ 4ቱ/ ከአንድ ብሄር ኦሮሞ ናችው፡፡ ወሳኙንና የሁለቱንም ችሎት አብላጫ ድምጽ ይዘዋል፡፡ ከላይ እንደተመለከተው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከፍተኛ የዳኝነት እና የመጨረሻ ውሳኔ ሠጭ አካል ከመሆኑ አኳያ የዳኞች የብሔር ስብጥር በራሱ ሊጤን የሚገባው አይደለም ወይ? እርግጥ ነው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚሠጠው የመጨረሻ ውሳኔ ከመሆኑ አኳያ፤ ይህ የሚሠጠው ውሳኔ በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው ላይ ከባድ አንዳምታ አንደሚኖረው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ፖለቲካም ሆነ ኢኮኖሚው ላይ ጠንካራ እጅ ያለው ፍርድ ቤት የብሔር ተዋጽኦ እንዴት ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።ክፍል( 2 ) ይቀጥላል….. https://youtu.be/wrcPF5jGQfw

Source: Link to the Post

Leave a Reply