You are currently viewing “የፌደራል ፖሊስ ገብቷል፤ የሚነካችሁ የለም በሚል ከጫካ ከተመለስን በኋላ የሚፈጸምብን ግድያ፣ እስር እና እንግልት ጨምሯል” ሲሉ የኖኖ ወረዳ ሚሊሾች ተናገሩ፤ በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል…

“የፌደራል ፖሊስ ገብቷል፤ የሚነካችሁ የለም በሚል ከጫካ ከተመለስን በኋላ የሚፈጸምብን ግድያ፣ እስር እና እንግልት ጨምሯል” ሲሉ የኖኖ ወረዳ ሚሊሾች ተናገሩ፤ በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል…

“የፌደራል ፖሊስ ገብቷል፤ የሚነካችሁ የለም በሚል ከጫካ ከተመለስን በኋላ የሚፈጸምብን ግድያ፣ እስር እና እንግልት ጨምሯል” ሲሉ የኖኖ ወረዳ ሚሊሾች ተናገሩ፤ በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በጅምላ ትጥቅ ለማስፈታት ያደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወም ጫካ የገቡ የአማራ ሚሊሾችና የግል ታጣቂዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። ዳሩ ግን “የፌደራል ፖሊስ ገብቷል፤ የሚነካችሁ የለም በሚል ከጫካ ከተመለስን በኋላ የሚፈጸምብን ግድያ፣ እስር እና እንግልት ጨምሯል” ሲሉ አማረዋል፤ የሚፈጸመው ድርብርብ በደልም በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል። እስሩ እና እንግልቱ ተጠናክሮ ከቀጠለባቸው አካባቢዎች መካከልም የኖኖ ወረዳ ዋና ከተማ ስልክ አምባ እና ማዞሪያ የተባሉ አካባቢዎች ይገኙበታል። በኦሮሚያ ልዩ ኃይል አማካኝነት መሳሪያቸው ተወስዶ ስልክ አምባ ላይ ከታሰሩት ከ20 በላይ የአማራ ሚሊሻዎችና የግል ታጣቂዎች በተጨማሪ በማዞሪያ ከተማ ልዩ ኃይሉ የሚሰጠውን የተሳሳተ መረጃን መሰረት በማድረግ የፌደራል ፖሊስ ከ12 በላይ ሚሊሾችን ማሰሩ ተነግሯል። ከእስሩ በተጨማሪም ህዳር 14 ቀን 2014 ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ በኖኖ ወረዳ የስልክ አምባ ፖሊሶች አቶ ይበልጣል ሽፋው በተባሉ ሚሊሻ ቤት በመሄድ አፈና ፈጽመዋል። እጅ ስጥ በማለት ተኩሰው ሽንጡ ላይ መተውታል፤ በሁለተኛው ጥይትም የመስሪያ ካዝናውን መተዋል፤ አቶ ይበልጣል ለጊዜው ተንከባለው ቢያመልጡም፤ የግድ ህክምና ማግኘት ስለነበረባቸው ወደ ጤና ጣቢያ ገብተው መሳሪያቸውን ለፖሊስ አስረክበዋል። ከዚህም በሻገር ህዳር 15 ቀን 2014 ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ አቶ በለጠ የተባለ ሚሊሻ ከቤቱ እያለ የከበቡት የተደራጁ ጽንፈኞች አባትዬውን ሲደበድቡ ተው እባካችሁ ብሎ በመለመኑ በጦር ተወግቷል፤ በገጀራ ተቆራርጦ በአደባባይ፣ በጠራራ ፀሀይ፣ የፌደራል ፖሊስ፣የኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ፖሊስ ባሉበት ከተማ በግፍ ተገድሏል። የደረሰና የታደገው አንድም የህግ አካል አልተገኘም፤ የታሰረና የተጠየቀ አካልም የለም ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአማራ ላይ የሚሰራው ግፍ ጫካ ባሉት ኦነጎች ብቻ ሳይሆን በመንግስት መዋቅር ጭምር የታገዘ በመሆኑ በአሳሳቢነቱ እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply