“የፌዴራል መንግሥት ህግ ለማስከበር በትህነግ ላይ እየወሰደ ያለውን  እርምጃ   እንደግፋለን።” የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ  አዴሃን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…  ጥቅምት 25 ቀን…

“የፌዴራል መንግሥት ህግ ለማስከበር በትህነግ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን።” የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 25 ቀን…

“የፌዴራል መንግሥት ህግ ለማስከበር በትህነግ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን።” የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለአለፉት አመታት ትህነግ /ህወሓት የአማራን ሕዝብ በጠላትነት በመፈረጅ ዘረፈ ብዙ ጥቃት ሲያደርስ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። ከማዕከላዊ መንግስት ስልጣን በህዝብ ትግል የተገፋ ቢሆንም በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል በመመሸግ ዳግም የማዕከላዊ መንግስትን ስልጣን ለመቆጣጠር የአማራን ሕዝብ ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ ሠላም እና ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል ነው ያለው አዴሃን በመግለጫው። በመሆኑም የፌዴራል መንግስት በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፍ ነው አዴሃን ያስታወቀው። በተጨማሪም መንግስት በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል ከፍተኛ ቀውስ እያደረሰ ባለው ኦነግ ሸኔ ላይም እርምጃውን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን ብሏል። የትነህግ /ህወሃት ወንጀለኛ ቡድን በህግ ቁጥጥር ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተከባበረ ክንድ እንዲወጣ ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድነቱን ማጠናከር አለበት ሲልም አሳስቧል። የፌዴራል መንግስት በተለያየ አካባቢዎች ለሚኖረው የአማራ ሕዝብ ጥበቃ እንዲያደርግለት እንጠይቃለን ብሏል። የትግራይ ሕዝብ የእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን የህወሃትን ቡድን ለህግ አሳልፎ በመስጠት ዛሬም እንደትናቱ ለኢትዮጵያ አለኝታነቱን እንዲያሳይ እንጠይቃለን ሲል ጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply