የፌዴራል መንግስት በህወሓት ላይ የወሰደው ግልፅ ያልሆነ አቋም አስደንጋጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( ኢዜማ) ባወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግሥት ሕወሓት ግጭቱን ለመቀጠል የወሰዳቸውን እርምጃዎች በግንባር ቀደምነት አመራር እየሰጠ ለማክሸፍ ከመሞከር ይልቅ ግጭቱ በክልሎች መካከል ያለ እስኪመስል የወሰደው ግልፅ ያልሆነ አቋም አስደንግጦኛል ብሏል፡፡

ሕወሃት የደቀነው አደጋ በሀገር አንድነትና ሰላም ላይ እንጂ በአንድ ወይንም በጥቂት ክልሎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ አይደለም ያለው ኢዜማ፤ አደጋውን ለመከላከል የሚወሰደው እርምጃ አንድ ወጥ የዕዝ ሰንሰለት ኖሮት በፌደራል መንግሥትና በኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት አመራር ሰጪነት ብቻ መወሰድ እንዳለበት ፓርቲው አስታውቋል።

በትግራይ ክልል ያለውን ችግር ሕወሓት ከደቀነው አደጋ አንፃር ብቻ በማየት ሕወሓትን ማሸነፍን ብቻ ዓላማ ያደረገ የአጭር ጊዜ ስልት ይዞ መቀሳቀስ ያስፈልጋል ያለው ፓርቲው፤ ከዚህ ባለፈ በዘላቂነት ክልሉ ወደ ተረጋጋ ሰላም እና ዜጎች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ሊመለሱ የሚችሉበትን አጭር ስልት ማስቀመጥ ያስፈልጋል ብሏል ።

ግጭቱ ለመጨረሻ ጊዜ ተቋጭቶ የሀገርን ህልውና እና አንድነትን በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚቻልበት ስልት የአካባቢውን ተወላጆች በማሳተፍ ተነድፎ ተግባራዊ መደረግ እንደሚያስፈልግም ፓርቲው ገልፃል ።

ቀን 12/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply