You are currently viewing የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አ…

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አ…

የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የፌዴራል መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በአስቸኳይ ያስቁሙ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አደረገ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መፍትሔ እንዲያገኙ:_ 1) በግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም፣ 2) ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም፣ 3) ግንቦት 28 ቀን 2014 ዓ.ም፣ 4) ሰኔ 14 ቀን 2014 ዓ.ም፣ 5) ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም፣ 6) ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም፣ 7) ጳጕሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም፣ 8) መስከረም 15 ቀን 2015 ዓ.ም፤ 9) መስከረም 20 ቀን 2005 ዓ.ም፣ 10) መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሁም 11) ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በተከታታይ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን በማውጣት የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲሰጡት ሲያሳስብ መቆየቱን አውስቷል። ይሁን እንጅ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ዜጎች ለከፍተኛ የሰው ህይወት መጥፋት፣ ለአካል ጉዳት፣ ለንብረት ዝርፊያና መውደም፣ ለእገታና መፈናቀል እየተዳረጉ ይገኛሉ ብሏል፡፡ 1) በኦሮሚያ ከልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከሳሲጋ ወረዳ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኝ ጽጌ ከተማ በጥቅምት ዐ8 እና 09 ቀን 205 ዓ.ም የታጠቁ ቡድኖች ባደረሱት ጥቃት ሞት፣ የአካል ጉዳት እና ንብረት ውድመት መድረሱን 2) በተመሳሳይ ጥቅምት 19 ቀን 205 ዓ.ም ከጊዳ አያና ወደ ነቀምት በሚወስደው መንገድ ላይ በህዝብ ትራንስፖርት ሲጓዙ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በአሁን ሰዓት ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውን እና የአካል ጉዳት መድረሱን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ ከጥቅምት 2 ቀን 205 ዓ.ም ጀምሮ ከነቀምት ወደ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና አሶሳ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ቦታዎች በሸኔ ታጣቂ ቡድን መዘጋቱን እንዲሁም የተዘጉ መንገዶችን እና በታጣቂ ቡድኑ የተያዙ አካባቢዎችን ለማስለቀቅ በታጣቂ ቡድኑ እና በመንግስት የጸጥታ አካላት መካከል በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ ንጹሀን ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም ከዓመታት በፊት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የነበሩና አንጻራዊ ሰላም አለ ብለው ወደ መኖሪያቸው በተመለሱ የጊዳ አያና ወረዳ ፊት በቆ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ በታጠቁ ቡድኖች ዘረፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑንም ገልጧል። 3) በኦሮሚያ ከልል ምስራቅ አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሑሩታ ዶሬ ቀበሌ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ/ም በሸኔ ታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት 4 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም እንዳሉና የቀበሌው ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ስጋት ላይ እንደሚገኙ፣ 4) በተመሳሳይ በጀጁ ወረዳ አምሻራ ቀበሌ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ላይ 8 ሰዎች በሸኔ መገደላቸውን እንዲሁም 5) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ፣ አዲስ ህይወት፣ መንበረ ህይወት፣ ተስፋ ህይወት፣ መርቲ እና አጫሞ ቀበሌዎች የሚኖሩ _ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂ ቡድኑ ተከበው በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን፣ 6) በተጨማሪም ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ 5 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂ ቡድኖች መገደላቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቅሷል፡፡ 7) በምዕራብ ሸዋ ዞን አማያ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም የሸኔ ታጣቂዎች በእርሻ ስራ የሚተዳደሩ 4 ሰዎችን አግተው ከወሰዷቸው በኋላ እያንዳንዳቸው ሶስት መቶ ሺህ ብር (300.000) ካመጡ ከእገታው እንደሚለቀቁ ተገልጾላቸው የታጋቾች ቤተሰቦችም ገንዘቡን አሰባስበው ሲሄዱ የታገቱት ሰዎች በሸኔ ታጣቂ ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ወሊሶ ፖሊስ ጣቢያ አስከሬናቸው እንደተገኘና ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም አስከሬናቸው ዘመዶቻቸው ወደሚገኙበት ተወስዶ የቀብር ስነ ስርዓታቸው መፈጸሙን ኢሰመጉ ለማወቅ ችሏል፡፡ 8) በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የሸኔ ታጣቂዎች ነቀምቴ ከተማ በመግባት ንጹሃን ሰዎች ላይ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዝርፊያና ሰዎችንም አግተው በመውሰድ አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ 9) ጥቅምት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ በሚወስደው የፍጥነት መንገድ ላይ ወደ መቂ ከተማ አካባቢ ታጣቂዎች በመንገዱ ሲጓዙ በነበሩ መኪናዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ጥቃት እንደፈጸሙ እና በዚሀም ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን፣ አካል ጉዳት መድረሱን እና በመንገዱ ሲጓጓዚ የነበሩ አንዳንድ መኪናዎቸ መቃጠላቸውን ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡ 10) በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊሚቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች ከሚኖሩበት አካባቢ ከ800 በላይ አባወራዎችን የሸኔ ታጣቂ ቡድን ወደ አካባቢው መጠጋቱን እና ከቦ መያዙን ተከትሎ መንግስት በፌደራል ፖሊስ በማጀብ ወደ ሌላ የጸጥታ ሁኔታው ወደሚሻልበት ቦታ ይዞአቸው መሄዱን ኢሰመጉ መረጃ መሰብሰቡን ገልጧል። በመጨረሻም ኢሰመጉ ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ የአካባቢዎቹ የደህንነት ሁኔታ ምቹ ሲሆን ሰፋ ያለ የምርመራ ስራን በመስራት ዝርዝር ዘገባን እንደሚያዘጋጅ ገልጧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply