የፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በቀን ከ6 ሺህ በላይ የሆኑ ሰነዶችን ህጋዊነታቸውን እያረጋገጠ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡
አገልግሎቱ ከፍትህ ስርዓቱ ጋር በተያያዘ ወንጀሎችን ለመከላከል በቀን ከ6 ሺህ በላይ ሰነዶች ህጋዊነታቸው ይረጋገጣል ሲሉ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደገቶ ኩምቤ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ባለፈው 2015 ዓ.ም ለ1.5 ሚሊየን ለሚሆኑ ተገልልጋዮች አገልግሎት መስጠት መቻሉን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ቢሮ የተቋቋመው በ1995 ቢሆንም ለረጅም ጊዜ የነበሩ አሰራሮቹ የሚያሰለቹ ፣ለወንጀሎች የተጋለጡ እና የሰነዶች ጥራት ችግር የነበረባቸው እንደነበር ጠቁመዋል።
ይህም ሀሰተኛ ሰነዶች እንዲፈጠሩ በማድረግ፣ሃገር በማጭበርበር ወንጀል ከፍተኛ ሃብት እንድታጣ ሲያደርጋት እንደነበር ገልጸዋል።
አሁን ላይ ግን አሰራሩ በዲጅታል እየታገዘ በመሆኑ ያንን ችግር በተወሰነ ደረጃ ማስቀረት መቻሉን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት 27 ከሚሆኑ ባንኮች እና ከ5 የመንግስት ተቋማት ጋር አገልግሎቱ በጋራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post