” የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ እናሳስባለን ” – ብላለች ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/JZwETAnYrWZwychuuWGKQbxuITPhFX9g4HkMp12V0KNWg1J1l3Jjg05_3caRTrmzO5nl0mU-z-R9TIUEzUz-O4JOaZsUkzKsr2tdPSytXf4VvGXmVR149M4ZeW_eT4IkvYrD2NgrKy5RA3K14ZXG9J4_2TihqWOm45_dUJH3GPchrlbirQLMuqBZH61Q4HcqT-Je_eWTcs7xLoDrWuHQg7hGwv1_J0RB0YYsmkEzdOzMsISmqlgKDtvVrcHdLdJfXR0IJ9IIIOk8EXbDM-IK-YcKryt25EdnsRlvzZiHiSYKGDZw2WKJrFjKKXjKVoSw3dpgzP1QfQsglJh3haokxw.jpg

” የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ እናሳስባለን ” – ብላለች ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ጥንታዊው እና ታሪካዊት ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም መሆኑን ገልጻለች።

በተለያዩ ጊዜያትም በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑንም አስታውሳለች።

አሁን ደግሞ 4 አባቶች በታጣቂ ቡድኖች ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ መሆኑን አመልክታለች።

አንድ አባት ደግሞ ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ይፋ አድርጋለች።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ ቤተክርስቲያኗ አሳስባለች።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply