የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ይካሄዳል

የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ የልዑካን ቡድን ጂግጂጋ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ የፌደራል የዴሞክራሲ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ ነው።

ሀላፊዎቹ ጂግጂጋ ጋራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማንና የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ መሎው ኢብራሂምን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የፌደራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ የምክክር መድረክ በአመት ሁለት ጊዜ እንደሚካሄድ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

The post የፌዴራል የዴሞክራሲ ተቋማት የጋራ የምክክር መድረክ ዛሬ በጅግጅጋ ይካሄዳል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply