የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የ4 ተጨማሪ ኩባንያዎች የባንክ ሒሳብ እንዲሁም ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር…

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የ4 ተጨማሪ ኩባንያዎች የባንክ ሒሳብ እንዲሁም ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር…

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የ4 ተጨማሪ ኩባንያዎች የባንክ ሒሳብ እንዲሁም ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን አገደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከዚህ ቀደም የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከህወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 34 ድርጅቶች የባንክ ሒሳብና ቋሚ ተንቀሳቃሽ ንብረት ማገዱ ይታወሳል፡፡ የታገዱት ኩባንያዎች ቁጥር 38 መድረሱን ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፍቃዱ ፀጋ ለሸገር ነግረዋል፡፡ ከ38ቱ ኩባንያዎች መካከል በስም መመሳሰል የኤፈርትን የኢሜል አድራሻ በመጠቀማቸው ከህወሓት ጋር ተዛምዶ ይኖራቸዋል በሚል ጥርጣሬ የባንክ ሒሳባቸው ታግደው ከነበሩት ኩባንያዎች ቢያንስ አንዱ ከዝርዝሩ ሊወጣ እንደሚችል አቶ ፀጋዬ ገልፀዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ኩባንያዎቹ ላይ የወንጀል ምርመራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ እገዳው በድርጅቶቹ ውስጥ ተቀጥረው የሚያገለግሉ ሰራተኞችን ሕይወት እንዳያመሰቃቅል ለድርጅቶቹ አዲስ አስተዳደር ተሹሞላቸው ስራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ነግረውናል ሲል ሸገር Fm ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply