የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በሙሉ ድምጽ ወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ የፌዴ…

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በሙሉ ድምጽ ወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የፌዴ…

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በሙሉ ድምጽ ወሰነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ካሳለፋቸው የተለያዩ ውሳኔዎች መካከል በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ያሳለፈው ውሳኔ ቀዳሚ ሆኖ ይገኝበታል፡፡ ውሳኔው የተላለፈውም በኢፌዲሪ ሕገ መንግስቱ አንቀጽ 62(9) ማንኛውም ክልል ሕገ መንግሥት በመጣስ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌዴራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል በሚለው ድንጋጌ መሰረት ስለመሆኑ ተገልጧል፡፡ በትግራይ ክልል ያለው ሕገ ወጥ ምክር ቤት እና ስራ አስፈጻሚም እንዲፈርስ፣ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ እንዲቋቋም፣ ይህ ጊዜያዊ አስተዳደር ደግሞ ስራ አስፈጻሚዎችን እንዲሾም የፌደሬሽን ም/ቤት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም በየሶስት ወሩ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ክልሉ ያለበትን ሁኔታ እንዲያሳውቁ የወሰነው የፌደሬሽን ም/ቤቱ ህገ መንግስታዊ ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድና ከፌዴራሉ መንግስት የሚሰጡ ትእዝዛትን እንዲፈጽም ሲል አክሎ ወስኗል። ከመከላከያ በህወሀት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃንም መላው ኢትዮጵያዊያን ከመከላከያ ጎን ቆመው እርምጃውን እንዲደግፉ ነው ጥሪ የቀረበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply