የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስትን አፈረሰ።ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የትግራይ ክልል በክልሉ በሚገኘው እና በአገር መከላከያ ሰራዊት ስር ባለው በሰሜን እዝ ላይ ጥቃ…

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግስትን አፈረሰ።

ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የትግራይ ክልል በክልሉ በሚገኘው እና በአገር መከላከያ ሰራዊት ስር ባለው በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው ብሏል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያከናውናቸዋል ተብሎ ከተሰጡት ስራዎች መካከልም
ሀ) አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤
ለ) የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤
ሐ) ሕግና ሥርዓት መከበሩን ያረጋግጣል፤
መ) አግባብ ባለው ህግ መሰረት በክልሉ ምርጫ የሚከናወንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
ሠ) የክልሉን እቅድና በጀት ያፀድቃል፤
ረ) በፌዴራል መንግስቱ የሚሰጡ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል ሲል ምክር ቤቱ አጽድቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply