
የፍትሕ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ምስጋን ዝናቤ ሀገር ጥሎ ተሰደደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 27/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ፍትህ መጽሄት በማህበራዊ ትስስር ገጿ እንዳስታወቀችው የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ምስጋን ዝናቤ ሀገር ጥሎ ተሰዷል። ጋዜጠኛው ሀገር ጥሎ እንዲሰደድ የተገደደውም በአገዛዙ ደህንነቶች ምክንያት ህይወቱ አደጋ ላይ በመውደቁ ነው በሚል ተገልጧል። በዚህ ምክንያትም የህትመት ስራዎቼን ለህዝብ ለማድረስ አስቸጋሪ አድርጎብኛል ስትል መጽሄቷ አስታውቃለች።
Source: Link to the Post