የፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር የባጃጅ አሽከርካሪዎችና የሆቴል ባለቤቶች ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለማስከበር እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና…

የፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር የባጃጅ አሽከርካሪዎችና የሆቴል ባለቤቶች ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለማስከበር እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና የሆቴል ባለቤቶች የሕልውና ዘመቻውን በድል ማጠናቀቅ በሚቻልበት ጉዳይ ከአመራሩ ጋር መክረዋል ። ሕዳር 21/03/2014 ዓ.ም (አሻራ ዜና) የባጃጅ አሽከርካሪዎች አቶ አንዷለም ታምሬና ባህሪው አናጋው ጠቅላይ ሚኒስትሪ ወደግንባር መዝመታቸው ልዩ ስሜትና ወኔ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል ። ለአካባቢያችን ሰላም መስፈን እኛም የድርሻችንን እንወጣለን ያሉት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስከበር ከጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሠሩ ናቸው ። የባጃጅ አሽከርካሪዎች በቀን አስር ብር ለሕልውና ዘመቻው ድጋፍ ለማድረግና ለጸጥታ አካላት ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ። የሆቴል ባለቤቶች አቶ ሀብታሙ ድልነሳ እና አቶ ሙሉነህ አምሳሉ በበኩላቸው ሰርጎ ገቦች እና ተላላኪዎች ሀገር ሰላም እንዳይሆን ብጥብጥ በመፍጠር አካባቢውን እንዳያውኩ የቅድመ መከላከል ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ነው የገለጹት ። የሕልውና ዘመቻው በድል እንዲጠናቀቅ የምናደርገውን ድጋፍም አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል ። የባጃጅ አሸከርካሪዎችና የሆቴል ባለቤቶች ከብዙ የማህበረሰብ ክፍል ጋር የመገናኘት እድላቸው ሰፊ በመሆኑ ለአካባቢ ሰላም ጸር የሆኑ ጉዳዮችን በመከላከል በኩል ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ዓለም አሳስበዋል ፡፡ የከተማው ማህበረሰብ በሁሉም ግንባር አከባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅና የኋላ ደጀንነት ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሠራ መሆኑንም አቶ ሙሉጌታ ገልጸዋል ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply