የፎገራ እና የሊቦ ከምከም አጎራባች ወረዳ እና ቀበሌዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ጥንቃቄ እና ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የፎገራ እና የሊቦ ከምከም አጎራባች ወረዳ እና ቀበሌዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ጥንቃቄ እና ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደቡብ ጎንደር ኮሚዩኒኬሽን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው የፎገራ እና የሊቦ ከምከም አጎራባች ወረዳ እና ቀበሌዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ አስፈላጊው ጥንቃቄ እና ትኩረት ተደርጎ መሰራት ይኖርበታል። ተቋሙ በፎቶ አስደግፎ እንደገለጸው የርብ ውሃ ሙላት ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል፤ ሙላቱም ከግድቡ አልፎ መሃል አስፋልትን አቋርጦ ሲያጥለቅለቅ ተስተውሏል። ስለሆነም የፎገራ እና የሊቦ አጎራባች ወረዳ እና ቀበሌዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት የሰው ሕይወት እንዳይጎዳ ጥንቃቄ የተሞላበት ህዝብን ወደ ተራራማ ቦታዎች ማስፈር እንደሚገባ ለሚመለከተው አካል አሳስቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply