የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለሰራተኞቹ ያሰራውን ዘመናዊ የጤና እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ጂምናዚየም አስመረቀ

የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለሰራተኞቹ ያሰራውን ዘመናዊ የጤና እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ጂምናዚየም አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስትም ይሁን የግል ተቋማት ሰራተኞችን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭነትን ለመቀነስ ምቹና ጥሩ የስራ አካባቢ መፍጠር ይገባል ተባለ፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለሰራተኞቹ ያሰራውን ዘመናዊ የጤና እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ጂምናዚየም ዛሬ አስመርቋል።

በኢትዮጵያ አጠቃላይ ከሚሞተው ሰው መካከል ከ52 በመቶ በላይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የችግሩ መበራከት ዋነኛ ምክንያትም በተለይ የቢሮ ሰራተኞች ለረጅም ሰአት ቁጭ ብለው ስለሚሰሩና እንቅስቃሴ ስለማያደርጉ ተላላፊ ላልሆኑ የተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣሉ።

በዚህ ምክንያት እንደ ስኳር፣ ደም ግፊትና ሌሎችም ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች እንደሚጋለጡ የጤና እና አካል ብቃት ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኞቹ በቅርበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ለማስቻል አካል ብቃት እንቅስቃሴ ጂምናዚየም አስመርቋል።

በምርቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የስፖርት ሳይንስ ባለሙያና የፊት ኮርነር አማካሪ ድርጅት መስራች አሰልጣኝ ነጻነት ካሳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ የጤናና አካል ብቃት እንቅሳቃሴ አሰልጣኞች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዳዊት አለባቸውም የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትን ተግባር አድንቀዋል።

የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት ትልቁ “ሰራተኞቻችን ደስተኛና ጤናቸው የተጠበቀ ሲሆን ህዝብን የማገልገል አቅማን ያሳድጋል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ለሰራተኞቹ ያሰራውን ዘመናዊ የጤና እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ጂምናዚየም አስመረቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply