“የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ፡፡
እማሆይ ፅጌማርያም በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ እንደነበሩ ይነገራል።
እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ከአቶ ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ወይዘሮ ካሣዬ የለምቱ በ1916 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውስጥ ነው የተወለዱት።
በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል።
ከትምህርት መልስም በ19 አመታቸው ነበር ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 አመታቸው ምንኩስናን የተቀበሉት።
ከ19 84 ዓ.ም ጀምሮ ኑሯቸውን በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ “ቅድስቲቷ ከተማ” ተብላ በምትጠራው እየሩሳሌም አድርገዋል።
አባታቸው ገብሩ ደስታ በኢትዮጵያ የከንቲባነት ታሪክ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን በአፄ ሃይለስላሴ ዘመንም የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን ማገልገላቸውን ታሪክ ያስረዳል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን