የፓሪስ ክለብ አበዳሪ እገራት ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር የብድር ስምምነት ላይ እንድትደርስ የሦስት ወራት ተጨማሪ ጊዜ መስጠታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል።አበዳሪ…

የፓሪስ ክለብ አበዳሪ እገራት ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር የብድር ስምምነት ላይ እንድትደርስ የሦስት ወራት ተጨማሪ ጊዜ መስጠታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል።

አበዳሪ እገራት ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር እስከ መጋቢት 23 ገደማ አዲስ የብድር ስምምነት ላይ ካልደረሰች፣ እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ያራዘሙላትን የብድር መክፈያ የእፎይታ ጊዜ ሊያጥፉት እንደሚችሉ አስጠንቅቀው ነበር።

ኾኖም ኢትዮጵያ እና ድርጅቱ በቀነ ገደቡ የብድር ስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸውን ተከትሎ፣ አበዳሪ እገራቱ ቀነ ገደባቸውን እስከ ሰኔ መጨረሻ ማራዘማቸውን ከምንጮች መስማቱን ዘገባው አመልክቷል።

የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ፣ የአበዳሪዎች ኮሚቴ ጊዜውን ማራዘሙን ኢትዮጵያ በደስታ እንደተቀበለችው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት በብድሩ ዙሪያ ከመንግሥት ጋር የሚደረገው ንግግር በተያዘው ወር መጨረሻ ዋሽንግተን ላይ እንደሚቀጥል ከትናንት ወዲያ መግለጡ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply