የፓርላማ የነገ ዉሎ፡- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገዉ እለት ከጠዋቱ 2፡00…

የፓርላማ የነገ ዉሎ፡-

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን በነገዉ እለት ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በም/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚያካሂድ አስታዉቋል፡፡
የስብሰባው አጀንዳዎችም፡-

1. በ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ማዳመጥ እና የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ በጀቱን አስመልክቶ የሚያቀርበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ማጽደቅ፣

2. የምክር ቤቱን 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ እና 6ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለጉባኤዎችን መርምሮ ማጽደቅ፣

3. የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ፣

4. የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች እና የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓስፊክ አገራት ድርጅት /አካፓድ/ የተቋቋመበት የተሻሻለውን የጆርታውን ስምምነት አስመልክቶ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ፣

5. የምክር ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደሚወያይ ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply