You are currently viewing የፓርቲው አመራሮች ለባለፈው ችግር የይስሙላ ይቅርታ እየጠየቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በወረደ አዲስ የማታለልና የማዘናጊያ ተግባር ላይ በመገኘት በየደረጃው ያሉ የድርጅቱን አመራሮችን፣ አባላትን፣…

የፓርቲው አመራሮች ለባለፈው ችግር የይስሙላ ይቅርታ እየጠየቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በወረደ አዲስ የማታለልና የማዘናጊያ ተግባር ላይ በመገኘት በየደረጃው ያሉ የድርጅቱን አመራሮችን፣ አባላትን፣…

የፓርቲው አመራሮች ለባለፈው ችግር የይስሙላ ይቅርታ እየጠየቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በወረደ አዲስ የማታለልና የማዘናጊያ ተግባር ላይ በመገኘት በየደረጃው ያሉ የድርጅቱን አመራሮችን፣ አባላትን፣ ደጋፊዎችንና ሕዝባችን ለማታለል እየሞከሩ ነው ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ተወካይ ኮሚቴ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ተወካይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ:_ የአብን ጠቅላላ ጉባዔ አባላት ተወካይ ኮሚቴ በጉባዔ ዝግጅት ሂደቱ ላይ ስምምነት መደረሱን ባሳወቀበት መግለጫ ዝርዝር ጉዳዮችን በየጊዜው እንደሚገልፅ ባስቀመጠው መሰረት ከዞን አመራሮችና የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ጋር ድርጅታዊ የሁኔታ ግምገማና ውይይት በማድረግ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የአብን 3ኛው ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ከሰብሳቢዎቹ መድረክ ረግጦ መውጣትና መቋረጥ በኋላ በጠቅላላ ጉባዔው አባላት ጥያቄም ሆነ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት በድጋሚ ተካሂዶ የተጀመሩት አጀንዳዎች እስካሁን ድረስ ውሳኔ ተሰጥቶባቸው መጠናቀቅ እንዳልቻሉ ይታወቃል፡፡ በጠቅላላ ጉባዔ አባላት ለአንድ ዓመት ሲደረግ ከነበረው የትግል ሂደት በተጨማሪ በቅርቡ ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት ጥረት መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ተወካይ ኮሚቴውም በነባር ከፍተኛ አመራሮች መካከል ያለውን ችግር ፈታን ማለታቸውንና ይቅርታ መጠየቃቸውን በመልካም የሚታይ እንደሆነ በመግለፅ የድርጅቱ ችግር መሰረታዊ መፍትሄ ግን በጠቅላላ ጉባዔው ሂደት የሚወሰን መሆኑን ታሳቢ በማድረግ “የጉባዔ ዝግጅት ኃላፊነቱ ከነባሩ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና ከጠቅላላ ጉባዔው አባላት ተወካይ ኮሚቴ መካከል በፍትሐዊነት በተዋቀረ ኮሚቴ እንዲከናወን ስምምነት የተደረሰ መሆኑን” የካቲት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ያሳወቀ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም ግን መጋቢት 2 ቀን 2015 ዓ.ም የድርጅቱ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች በባህር ዳር ከተማ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አደረግን በማለትና የጋራ የጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴ ማቋቋም የሚለውን በሽማግሌዎቹ ምክረ ሃሳብ መሰረት ስምምነት የተደረሰበትን ጉዳይ ወደ ጎን በመተውም ሆነ ህጋዊ ያልሆነ ውክልና በመስጠት ክህደት ፈፅመዋል፡፡ ከአሁን በፊት እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጉባዔ እንዲያዘጋጁ ተመርጠው የነበሩ፣ ከተሰጣቸው ኃላፊነት ውጭ ካልታወቀ የፋይናንስ ምንጭና ከፓርቲው የፋይናንስ አሰራር ውጭ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ በማዋል በተለያዩ ከተሞች የፓርቲውን የዞንና የወረዳ መዋቅር አመራርና የጠቅላላ ጉባዔ አባላትን እየሰበሰቡ :_ 1) በአካባቢ/በጎጥ የመከፋፈል ስራ ሲሰሩ በታችኛው መዋቅር ከፍተኛ ትግል/ተቃውሞ ያጋጠማቸው፣ 2) ከደንብና መርህ ውጭ የጥቂት ግለሰቦችን ፍላጎት መሰረት አድርገው ዋናውን የጉባዔ ዝግጅት ሂደቱን በድብቅ ለማከናወን ሲጥሩ የነበሩ፣ 3) ሂደቱ የግልፅነትና የመርህ ችግር ስለታየበትና መሻሻል ስላልቻለ የተወሰኑ የኮሚቴ አባላት ራሳቸውን ያገለሉበት፣ 4) በድርጅት ያልፀደቀ ሰነድ ለምርጫ ቦርድ እስከማስገባት የደረሱ እና በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ኃላፊነታቸውን አጠናቀው ጉባዔውን ማሳካት ያልቻሉ አካላትን አሁንም የጉባዔ አዘጋጅ አድርጎ እንደገና አፅድቄያለሁ ብሏል፡፡ ይህን ከፓርቲው ፕሮግራም፣ ስትራቴጂ፣ ደንብና መርህ ውጭ የተከናወነ እንቅስቃሴን እውቅና ለመስጠት የተደረገው ጥረትና ቀሪ ተግባራትን አጠናቀው ጉባዔ እንዲደረግ አስወስነናል ማለታቸው እስካሁን “ለተፈጠሩት ችግሮች ይቅርታ እንጠይቃለን” የሚሉት የለበጣና ጊዜያዊ ማታለያ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህ አካላት ከድርጅታችን አሰራር ባለፈ ለሕዝባችን ግብረ ገባዊ መርሆዎች ፈፅሞ ተገዥ መሆን የማይችሉ መሆናቸውን የሽምግልና ቃል በመካድ በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡ በአንድ በኩል ለባለፈው ችግር የይስሙላ ይቅርታ እየጠየቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ደረጃ የወረደ አዲስ የማታለልና የማዘናጊያ ተግባር ላይ በመገኘት በየደረጃው ያሉ የድርጅታችን አመራሮችን፣ አባላትን፣ ደጋፊዎችንና ሕዝባችን ለማታለል መሞከራቸው እጅግ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ከመሆኑም በላይ አሁን ያሉበት ሁኔታ ድርጅታችንንም ሆነ ትግላችንን ለመታደግና ወቅቱ በሚጠይቀው ደረጃ ለማጠናከር ዝግጁ አለመሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡ ተወካይ ኮሚቴው ይህን ሁኔታ ለምርጫ ቦርድና ለሽማግሌዎች በቃል ከመናገር ባሻገር በደብዳቤ እንዲያውቁት አድርጓል፡፡ እነዚህ አመራሮች ማንኛውንም ድርጅታዊ ውክልናና እንቅስቃሴ ማድረግ የሚያስችላቸውን ህጋዊ ስልጣንና መዋቅራዊ ቅቡልነት በራሳቸው ጊዜ ቀርጥፈው የበሉ በመሆናቸው ማለትም፡- 1) የምርጫ ቦርዱ ህጋዊ አለመሆናቸውን ውሳኔ ሰጥቶበት የነበረና ለድርጅቱ አመራሮች ሲል እንደገና እውቅና የሰጣቸው ከመሆኑ ባሻገር ከመጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም የጉባዔው መቋረጥ ቀጥሎ በእነዚህ አካላት የሚገኙ አመራሮችን መተማመኛ ድምፅ የመንፈግ ፊርማ በጉባዔው አባላት የቀረበባቸው በመሆኑ፤ 2) የምርጫ ቦርዱ እስከ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ጉባዔው ተደርጎ የአመራር ለውጥ (ሪፎርም) እንዲያደርግ ውሳኔ ቢሰጥም ተግባራዊ አለመደረጉና የእነዚህ አካላት ህጋዊነት ያልፀደቀ በመሆኑ፤ 3) የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በተደረገው ጉባዔ ላይ በፀደቀው የድርጅታችን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለ3 ዓመታት ያህል የተሰጣቸው የስልጣን ዘመን የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም በመጠናቀቁ እና ከየካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ህጋዊ ስልጣንና ኃላፊነት የሌላቸው በመሆኑ ጉባዔ ማዘጋጀትን ጨምሮ ማንኛውንም ድርጅታዊ እንቅስቃሴ ለማካሄድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አለመኖሩ፤ 4) በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወሩ ድርጅታዊ ያልሆኑ ስብሰባዎችን በተደጋጋሚ በማካሄድ የድርጅታችን ግብና መርህ በሚፃረር ሁኔታ አመራሮችን፣ አባላትንና ሕዝብን የሚከፋፍል የጎጥ ኢንዶክትሪኔሽንና አሰላለፍ ላይ ተሰማርተውና አሰማርተው የቆዩ አመራሮች ያሉበት በመሆኑና የተወሰደ ድርጅታዊ የእርምት እርምጃ አለመኖሩ፤ 5) የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርት ለሚመለከተው የድርጅቱ አካል ማቅረብ አለመቻልና በድርጅት ያልፀደቀ የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርትን በመጠቀም ድርጅቱን ለአደጋ በማጋለጥ፤ 6) የድርጅቱ ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነውን የጠቅላላ ጉባዔውን ጥያቄና አቅጣጫ ለመቀበል ፈቃደኛ ካለመሆን አልፈው ከድርጅቱ ደንብ በተፃራሪ ራሳቸውን የበላይ የስልጣን አካል የማድረግ እንቅስቃሴ ላይ በመገኘታቸው፤ 7) በጠቅላላ ጉባዔ አባላት የተወከለ አካል እያለ የስራ ዘመናቸው ከመጠናቀቁ፣ በጠቅላላ ጉባዔው እውቅና ከመነፈጋቸው እና የተቋረጠውን ጉባዔ ሳያጠናቅቁ ከአንድ ዓመት በላይ ከማስቆጠራቸው ባለፈ የድርጅታችን አመራሮችን፣ አባላትን፣ ደጋፊዎችንና ሕዝባችን በአዲስ መልክ በማታለል ለመቀጠል እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸው፤ ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ሁሉ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ አግኝንተነዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply