የፓኪስታኑን መስጊድ ያፈነዳው ግለሰብ የፖሊስ ልብስ ለብሶ ነበር

https://gdb.voanews.com/800f0000-c0a8-0242-9299-08db0472a9cd_w800_h450.jpg

ባለፈው ሰኞ፣ በፓኪስታኑ የኺበር ፓኽቱንዃ ክፍለ ግዛት፣ ፔሻየር ከተማ በሚገኘው መስጊድ ላይ ባደረሰው የአጥፍቶ መጥፋት ፍንዳታ 101 ሰዎችን የገደለውና 150 ሰዎችን ያቆሰለው ግለሰብ የፖሊስ ደንብ ልብስ ለብሶ እንደነበር ተነገረ፡፡

በቦታው በነበረው የቪዲዮ ምስል እንደታየው አጥፍቶ ጠፊው ጥብቅ ጥበቃ ይደረግለት የነበረውን የፖሊስ ኬላ ያለምንም ችግር አልፎ፣ በሞተር ብስኬሌት ወደ ውስጥ መዝለቁ ተነግሯል፡፡

ይህ ሲሆን ጠባቂዎች ማንነቱን ለማጣራት ምንም ዓይነት ሙከራ አለማድረጋቸውንም የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply